ግን ጋይስ ፀሎት አደርጋለው ሁሌ ፈጣሪን ግን አይሰማኝም ለምንድነው ጋይስ ግራ በተጋባውበት ጊዜ ብቻ እኔ እንጃ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም እስኪ መልሳቹ ምንድነው ጋይስ ንገሩኝ
Apr 27, 2026ጥያቄዎችን ልጠይቅህ?😁ጸሎት የምታደርገው የሆነ መልስ እንዲመለስልህ ብቻ ነው? ጸሎት ካረኩኝ መልስ ማግኘት አለብኝ ብለህ ታስባለህ? ብዙ ጊዜ የምንሳሳታቸው ነገሮች ፈጣሪን በቃ እንደ ሞኙ ጓደኛ አድርገን ቆጥረን ከዛ ጸሎት ካረግን ወዲያው እንዲመለስልን እናስባለን። ጓደኛህን ገንዘብ ካልሰጠኸኝ እኔ ካሁን ወዲህ ካንተ ጋር አልነጋገርም ወይ ምናምን እንደማለት። አንተ ለፈጣሪ ምን አርገህለታል? የምመክርህ ነገር ለጥቅምህ ስትል ብቻ ጸሎት አታድርግ እንደገና ደግሞ ጸሎትህ መዘግየቱም ሆነ አለመመለሱ ለራስህ ጥቅም ሊሆን የሚችልበት ጊዜ አለ
Apr 28, 2026