ጥያቄ፡- በታማኝነት ዙሪያ ምክር እፈልጋለሁ ከአሁኗ ፍቅረኛዬ ጋር ፍቅር ከመጀመራችን በፊት የቅርብ ጓደኛሞች ነበርን። በወቅቱ ሌላ ፍቅረኛ ነበራት፤ እኔም እንደ ጓደኝነታችን "ብቻችሁን ስትሆኑ ስህተት ሊፈጠር ስለሚችል ተጠንቀቁ" ብዬ እመክራት ነበር። እሷ ግን "ምንም አይነት ነገር አይፈጠርም፣ ድንግል ነኝ" ብላ ትነግረኝ ነበር። በኋላ ላይ ግንኙነታቸውን አቋርጠው እኛ ፍቅር ጀመርን። ነገር ግን ፍቅር ከጀመርን በኋላ ያኔ የነገረችኝ ውሸት እንደነበርና ድንግልናዋን በ16 ዓመቷ እንዳጣች ነገረችኝ። ላለማስቀየም "ችግር የለውም" ብያት ብናልፈውም፣ ውስጤ ግን ሰላም አጥቷል። እሷን በጣም እወዳታለሁ፣ ግን ያኔ መዋሸቷ እና በዛ እድሜዋ ያጋጠማት ነገር በአምሮዬ እየተመላለሰ ሊያሳርፈ አልቻለም። ከራሴ ጋር እየታገልኩ ነው። ምን ትመክሩኛላችሁ? ይህን ስሜት እንዴት ላሸንፈው እችላለሁ?
Apr 25, 2026ኢትዮጽያ ዉስጥ ከግማሽ በላይ ሴቶች እንዲ ነዉ የሚሉት ወዳጄ ጭራሽ የኔዋ ድንግል ነኝ ቡላ ግንኙነት ስናረግ አደለችም እና ገርሞኝ ስጠይቃት ምን ብትል "ደማነስ ስላለብኝ ደም አይኖረዉም" ድፍረቷ በጣም ገርሞኝ አብሬአት ነኝ
Apr 25, 2026