Heyy እንዴት ናቹ? በጣም የድሀ ልጅ ጥሩ ጭንቅላት ያለው የቤተሰብን ችግር ለመፍታት የምሞክር ሰዉ ነኝ ግን ዛሬ መጠየቅ የፈለኩት በህይወት በጣም ፈተና በዛብኝ ሲቀጥል 4 ወይም 5 ግዜ በጣም ህይወቴን ሊቀይሩ የሚችሉ ነገሮችን ሞክሬ ብዙ ዋጋ ከፍዬ ጫፍ ላይ ሲደርስ ይበላሽብኛል ምን እንደሆነ እንኳን ችግሩ አይገባኝም በቃ በዚ ምክንያት ነገሮችንም መሞከር ልተው ነው የምትሉኝ ነገር ካለ....
Apr 23, 2026ንስሐ ገብተህ ፀበል ተጠመቅ ቅርብህ እና የምትታመነው ታቦት ስም ያለ ፀልይ ተሳልም። ከዚህ የተረፈው ሰው ሰውኛው ደግሞ... የሐብታምም ልጅ ሆኖ 10ጊዜ ሞክሮ በ11ኛውም የማይሳካለት አለ ፤ ደጋግመህ ሞክር ከባለፈው ስህተትህ ቁጭ ብለህ እንደ ስራ ትምህርት ውሰድበት አብዛኞቻችን አናደርገውም ስራ ስለቀየርን ችግሩ የሚቀየር ይመስለናል ግን አይደለም ክፍተታችን በቶሎ የማይቀየር ካልሆነ ለቦታው የሚመጥን ሰው እስካልቀጠርን ድረስ። ካንተ አንድ ሁለት እናም በጣም በቢዝነስ ራመድ ካሉ ሰዎች ጋር ዋል ተሞክሮ ውሰድ አብረህ መስራት የምትችልበት እድሎችን ቶሎ ተቀበል እናም ፈልግ በተረፈ ስራ ሊያሰሩህ የሚችሉ ሰዎች በዙሪያቸው ስለሚኖሩ እንዲያገናኙህ ወትውት።
Apr 23, 2026