ከረጅም ጊዜ በኋላ ለሊት ላይ ወደ ቲክቶክ መንደር አቀናው ! የሰርግ ወቅት ስለኾነ እንደው እንጃ ስብከቱ ስለ ትዳር ዝማሬው ስለ ከብካብና ስለ መሰል ጉዳዮች ኾኖ ተመለከትኩ። እህቶች ግን ምን ነካችኹ ? ! ተሽሞንሙኖ በነጠላ ፎቶ እየተነሱ የወደፊት ባሌ የቅዱስ እከሌ ወዳጅ መኾን አለበት ፤ ባሌ ሰርጋችንን እዚኽ ገዳም ጫጉላችንን እዚኽ ፤ በዚኽ ጊዜ እንቆርባለን እንዲ እናስቀድሳለን ፤ እኔ ከባሌ መኪና ቤት ምናምን አልፈልግም ፤ ዲያቆኔ አንተን ባየ ዐይኔ ፤ የሰርጌ ቀን የምዘምረው ፤ እኔ እሱ ፤ ቅብጥርስዮ ምንትስዮ እያላችኹ የምትንዘባዘቡት ? ስትቆርቡ የቆረባችኹበትንም ኾነ የምትቆርቡበትን ልብስ እንደለበሱ "ዛሬ ደስ ብሎኛል" ምናምን እያሉ መቅደስ ውስጥ ፎቶ እየተነሱ ቪዲዮ እየቀረጹ መልቀቁ ለምን አስፈለገ ? ምንድነው ዓላማችኹ እንዲኽ የምታደርጉ ሴቶች ? እምነትን ሽፋን ያደረገ የጥበሱኝ ቅስቀሳ እንደኾነ እናውቃለን ! ! ( እናንተ መንፈሳይ ( መንፈሳዊ አላልኩም ) መኾናችኹ ሳያንስ እናነትን ለመጥበስ የሚመጣውን ወንድ የአምልኮ መልክ እንዲኖረው ኃይሉን ግን እንዲክድ ለምን መንገድ ትጠርጋላችኹ ? # ወንዶች ወደ ክርስቶስ መቅረብን ትፈልጉታላችኹ ? እንዲኽ ካሉት ሴቶች ራቁ ! ! ( ሴቶች ! በአንደበታችኹ መንፈሳዊነት በቲክቶክ ላይ እንደምትኾኑት አይደለም ! የዲያቢሎስ ውጊያ ከኢራን እና ከእስራኤል ውጊያ የከፋ ነው ! እረፉ ትጠፉበታላችኹ በዝምታ መዳን ጥቂት በጥቂት ማደግ በጥበብ መመላለስ ለምታደርጉት ነገር ኹሉ ከመጽሐፍ ምስክር ማቆም ! በጎውን ተግባር እንኳ በመንፈስ መመርመር ልመዱ !
Apr 21, 2026ደግሞ ዘማሪዎቹ " እቴ መርዓት አዳም አጥባት " የምትሉት ኧረ ነውር ነው ስለፈጠራችኹ ! ! ሰንበት ተማሪዎች እባካችኹ የሰማችኹትን ኹሉ አትዘምሩት መጠየቅ ልመዱ መምህራንን ! ! ከሰይጣን ይልቅ ልማድ ክፉ ነው ! " ዐውደ ምሕረት ላይ ካህናት ወረብ ከሰሩ በኋላ ሰንበት ተማሪዎች ወረብ ሊያቀርቡ ሲሉ " በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተተኩልሽ " የሚል ያለ ቦታው የሚገባ ጥቅስ በኹሉ እንደተለመደ ኹሉ እባካችኹ የሚባልን እና የማይባልን እወቁ ጠይቁ። በግሌ ስለቤተክርስቲያን ማየትም መስማትም መወያየትም ያቆምኩት በብዙ ምክንያቶች ሲኾን አንዳንዴ ግን እንደው ተሳስተን ስንገባ ተስፋ የሚያጭር ነገር እንድናይ ብትፈቅዱልን እባካችኹ ! !
Apr 21, 2026(edited)