"ማቴ 1:25 የበኽር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፣ ስሙንም እየሱስ አለው።" anyone who is able to brief me on this please! From orthodox perspective since I am orthodox too.
Apr 14, 2026አላወቃትም የሚለው አዳም ሔዋንን ባወቀበት ግብር አላወቃትም ማለት ነው። በዚህ ጊዜ "እስክትወልድ" ሲል ከወለደች በኋላ አወቃት ማለት አይደለም። ይህ "እስከ" ፍጻሜ የሌለው እስከ ነው። ሜልኮል እስክትሞት ድረስ ልጅ አልወለደችም ካለው ጋር ተመሳሳይ ነው። ሁለተኛው ድንግል ማርያም ጌታን በፀነሰችው ጊዜ መልኳ ይለዋወጥ ነበር። እስክትወልድ ድረስ በቋሚ መልክ አላወቃትም ነበር ማለት ነው። ከወለደች በኋላ ግን በቋሚ መልክ አውቋታልና ነው። ሦስተኛው ነቢዩ ኢሳይያስ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ብሎ የተናገረላት እርሷ መሆኗን እስክትወልድ ድረስ አላወቀም ነበር ማለት ነው።
Apr 14, 2026