899898436.5
#religion
ለኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች እንኳን አደረሳችሁ ኪላላይሶን ምን ማለት ነው እና ደሞ ለምንድነው ዛሬ ቀን ተደጋግሞ ሚባለው?
Apr 10, 202610 engagements
ለኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች እንኳን አደረሳችሁ ኪላላይሶን ምን ማለት ነው እና ደሞ ለምንድነው ዛሬ ቀን ተደጋግሞ ሚባለው?
Apr 10, 2026በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ የውጭ ቃላት አሉ ቀጥታ ሳይተረጓሙ ከዕብራይስጥ፣ቅብጥ፤ግሪክ ቃላት ይገኛሉ። ኪርዬ ኤሌይሶን/ኪርያላይሶን/ ኪርዬ ማለት እግዚኦ ሲሆን ኪርያ ሲሆን ግን እግዝእትነ ይሆናል ኪርያላይሶን የምንለው በተለምዶ ነው እንጂ መባል ያለበት ኪርዬ ኤሌይሶን ነው ትርጉሙም አቤቱ ማረን ማለት ነው። እብኖዲ ማለት አምላክ ማለት ነው። ናይናን ማለት ማረን ይቅር በለን ማለት ነው። ታኦስ የግሪክ ቃል ሲሆን ጌታ አምላክ ማለት ነው። ማስያስ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ መሲሕ ማለት ነው ትስቡጣ ማለት ዴስፖታ ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ደግ ገዥ ማለት ነው። ኢየሱስ ማለት መድኃኒት ማለት ነው። ክርስቶስ ማለት መሲሕ ማለት ነው። አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው። ይቀጥላል.....
Apr 10, 2026(edited)የግሪክ ቃሌ ነው ኬሪያ( ኪሪወስ) = ጌታ ኤሌይሶን = አቤቱ ማረን
Apr 10, 2026😇😇
Apr 10, 2026እንኳን አደረሰን ጌታ ሆይ ማረን ማለት ነው ምህረት ለመጠየቅ
Apr 10, 2026😇😇
Apr 10, 2026ለምን በዚህ ቅርን ተመረጠ
Apr 10, 2026I think this was the day Christ was crucified on the cross.
Apr 10, 2026