. የአካዝያስ ዕድሜ (፪ ነገሥት ፰፥፳፭ እና ፪ ዜና ፳፪፥፪) ጥያቄው፦ ነገሥት ላይ 22 ዓመቱ ነው ይላል፣ ዜና መዋዕል ላይ ደግሞ 42 ይላል። መልስ፦ ይህ የቁጥር ልዩነት የመጣው ከቆጠራ ሥርዓት ልዩነት ነው። ፪ ነገሥት ላይ የተጠቀሰው 22 ዓመት አካዝያስ በራሱ ስም መንገሥ የጀመረበትን ትክክለኛ ዕድሜውን ይገልጻል። ፪ ዜና ላይ የተጠቀሰው 42 ዓመት ግን የአባቱ የኢዮራም ቤተሰብ (የአክዓብ ቤት) መንገሥ ከጀመሩበት ዘመን ጀምሮ ያለውን ድምር ውጤት የሚገልጽ ነው። ይህም የአክዓብ የክፋት ዘር በይሁዳ መንግሥት ላይ ሥልጣን የያዘበትን "የቤተሰቡን የንግሥና ዕድሜ" እንጂ የግለሰቡን ዕድሜ ብቻ አይገልጽም። (አንዳንድ ሊቃውንት ደግሞ የትርጉም ወይም የጸሐፊ ስህተት ሊሆን እንደሚችልና ዋናው የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ግን ድነት መሆኑን ያስረዳሉ)። ፪. ስለ ይሁዳ ሞት (ማቴዎስ ፳፯፥፭ እና የሐዋርያት ሥራ ፩፥፲፰) ጥያቄው፦ ማቴዎስ "ታንቆ ሞተ" ይላል፣ የሐዋርያት ሥራ ደግሞ "ተዘቅዝቆ ወድቆ ተሰነጠቀ" ይላል። መልስ፦ ሁለቱም ታሪኮች እርስ በርሳቸው ይደጋገፋሉ እንጂ አይጋጩም። ይሁዳ መጀመሪያ ራሱን አንቆ ሰቀለ (እንደ ማቴዎስ አገላለጽ)። ነገር ግን የሰቀለበት ገመድ ወይም ዛፍ ተበጥሶ/ተሰብሮ አስከሬኑ መሬት ላይ ሲወድቅ ሆዱ ተቀዶ አንጀቱ ፈሰሰ (እንደ ቅዱስ ሉቃስ አገላለጽ በሐዋርያት ሥራ)። አንዱ የሞቱን መጀመሪያ (ማነቁን)፣ ሌላኛው ደግሞ ከሞቱ በኋላ የሆነውን ክስተት ገልጠዋል። ፫. "ወልድ ያችን ቀን አያውቃትም" (ማርቆስ ፲፫፥፴፪) ጥያቄው፦ ክርስቶስ አምላክ ከሆነ እንዴት ያችን ቀን አያውቅም? ዘዳግም ፳፪፥፳፱ (ስለ 50 ሰቅል ብር) ጥያቄው፦ ይህ ሕግ ሴቶችን ይበድላል? can any one explain this concept
Apr 07, 2026@272114 ሰፋ ያለ ነገር እልክልሃለው እዚህ የተገደበ ነው ለመጻፍ
Apr 07, 2026