ሰላም ሰዎች አንደ የቤተሰብ ችግር ገጥሞኝ እንድታማክሩኝ ነበር .. እሱም ከስድስት አመት በላይ ጓደኛ አለኝ አብረን ብዙ ነገር አሳልፈናል ብዙ ነገር ሆነናል አድርገናል እብርን ያላደረግነው ያልሆነው ነገር የለም በሁለታችን ጓደኝነት ምክንያት ራሱ እናቶቻችን በጣም ተግባብተዋል አሁን ደግሞ የጋራ ንግድ ጀምረን እየሰራን ነው። ወደዋናው ጉዳይ ስመጣ ይህ ጓደኛዬ የውጪ process ጀምሮ ነበር እና interview አዲስ አበባ ተጠራ ሁሉንም ነገር አብረን አጣራን ከዛ አብረን እንሂድ ከኔ አንተ የተሻለ ታቃታለህ እና አብረን እንሂድ አለኝ .እኔም በነዛ ሁለት ቀናት ውስጥ ማረገው ነገር ስለየለ እሺ እንሂድ ችግር የለውም አልኩት ከዛ እቤት ስናገር እናቴ በጣምም ተቆጣች ያለውን ነገር ሁሉ አስረዳዋት እንደውም ነገርኳት ይባስ ተናደደችና ለምን ትሄዳለህ ምናገባህ ብላህ ማድሆኑ ስድቦችን ሰደበችኝ ነገሩን ወደ ራሴ ህይወት አምጥታው ብዙ ሰደበችኝ እና አያገባኝም ገደል ግባ አለችኝ ... (Even ሙል ወጪውን እሱ ነው ሚችለው) አንተ ካልሄድክ ብቻዬን እንዴት ሄዳለው ማላቀው ሀገር ብሎኝ ጭርሽ ሊቀር የነበረውን ነው በጣምም ገፋፍቼው እንድንሄድ ያሳምንኩት በዚህ ማሀላ እናቴ ደግሞ... እንደ ህፃን ነው ምታየኝ ግን 23 አመቴ ነው ( ለ ቤተሰብ ሁሌም ልጅ ልጅ ነው ግን ይህ ....)ምን እንደማረግ አላቅም እባካቹ አማክሩኝ በማርያም!! በጣም ነው ክብድ ያለኝ ምን እንደምወስን
Apr 06, 2026ለእናትኽን የሚቀርቡ ትልቅ ሰው ካሉ ለእነሱ አስረዳና እንዲያሳምኑልኽ አድርግ!
Apr 06, 2026