በቤተ ክርስቲያን ክህነት ደረጃዎች እና ሌላ ምናልባት ሌሎች የክብር አጠራሮች አሉ? ለምሳሌ መላከ ሰላም ቆምስ እገሌ ሲባል ፣ መላከ ሰላም ምንድን ነው ? ቆምስ የክህነት ደረጃ እንደሆነ አውቃለሁ ። ሌላ መምህር እንደ ክህነት ሲጠራም ሰምቻለሁ ፣ ዲያቆን ሆኖ ደም መምህር ሲባልም አይቻለሁ ። እሲኪ በግልግ የሚያስረዳኝ
Apr 06, 2026መልአከ ሰላም፣ መልአከ ገነት፣ መልአከ ምሕረት....የመሳሰሉት ለአስተዳዳሪዎች የሚሰጥ ነው። መልአክ ማለት አለቃ አስተዳዳሪ ተብሎም በቁም ፍቺ ይፈታል። ለዚህ ማሳያ ራእይ ዮሐንስ ላይ ለሰርምኔሱ መልአክ... እያለ ለ7ቱ ይጻፍላቸዋል። እና ለምሳሌ ደብሩ አንቀጸ ምሕረት ከሆነ አስተዳዳሪው መልአከ ይሆንና ምሕረት የሚለውን ወስዶ መልአከ ምሕረት ይባላል።
Apr 07, 2026