Lehemamat mndnw mareg yalebgn ena metselyews tselot .....madreg yelelebgns neger mndnw
Apr 05, 2026በሰሙነ ሕማማት የማይፈቀዱ/የማይደረጉ/ ነገሮች እኒህ የተከለከሉበት ምክንያት ስለ ሁለት ነገር ነው፦ የጌታን መከራ ለማሰብ የብሉይ ኪዳንን ወቅት ለማስታወስ - መስቀል መሳለም/ማሳለም/፤ ፀበል መጠመቅ የለም። - ቅዳሴ የለም ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር - አብዝቶ መደሰት። - በአልጋ አንድ መሆን/ግብረ ሥጋ ግንኙነት/። - ካለ ልክ መብላት/ዝክር የለም/። ግዴታ ማድረግ ያለብን - ወደ ቤተክርስቲያን መጥቶ ከክርስቶስ መከራ መሳተፍ ማለት ግብረ ሕማሙን መስማት እና መስገድ በሕማማት ከቤተክርስቲያን እየተቻለው ችላ ብሎ የሚቀር ክርስቲያን ቁጥሩ ክርስቶስን ከሰቀሉ ከአይሁድ ነው። - ጾም እስከ የቻለ እስከ ምሽት 1:00 ድረስ ይጹም። -የክርስቶስን መከራ ለጥቂት ደቂቃ እንኳን ቢሆን ማሰብ። ማሳሰቢያ፦ * ሰላምታ አልተከለከለም ፤ ጸሎትም ቢሆን በግል የሚጸለየው ገደብ የለውም።
Apr 05, 2026