ሰላም መንጃ ፋቃድ በተመለከተ ትልቅ ችግር አለ.. አንድ ሰልጣኝ ሙሉ ስልጠና ሳይወስድ ለፈተና ማቅረብ? ተገቢ ነው? እኔ ለምሳሌ መሰናክል ሳያሳየኝ.. ወደ ፈተና እንድቀርብ እያደረገኝ.. መሰናክል ሳልሰራ መፈተን ማለት ብዙ Point እጥላለው ማለት.. ከዛ ነጥቤ ዝቅ ሲል... ብር ክፈል እና ታልፋለክ ነው ነገሩ.. በጣም ብዙ ሰው ብሩን እየተበላ ነው.. Head office ደውይ ነበር.. እነሱም ግን ስልክ ከመስጠት ውጪ መፋትሄ አልሰጡኝም አመሰግናለሁ @
Apr 01, 2026Brother መብትህ ነው በደንብ ሳልለማመድ አልፈተንም ማለት። እኔ በደንብ ሳልለማመድ ተፈትኜ ሁለቴ ወደኩኝ። ሶስተኛ ለመፈተን ስል አመት አልፎሀል ብለው ግማሽ ክፍያ 8000 ብር አስከፈሉኝ። አሁን እራሳቸው አምስት ቀን አለማምደው ለሶስተኛ ጊዜ ልፈተን ነው። ስለዚህ ማንንም እንዳትሰማ። የመለማመጃ ቀንህ ቢያልቅ ራሱ በራስህ እርግጠኛ ካልሆንክ መጠየቅ ትችላለህ እምቢ ካሉህ በግልህ ተለማምደህ ግባ። ደግሞ መሰናክል ካልቻልክ እንደምትወድቅ እርግጠኛ ሁን። አብዛኛውን mark እሱ ነው የሚይዘው። አሰልጣኝህ ሌላውን ትቶ እሱን ብቻ እንዲያሳይህ ንገረው። ሌላው አይከብድም። የጓደኛዬ አሰልጣኝ ከአስራ አምስት ቀን በላይ መሰናክል ነበር ሲያስተምረው የነበረው እና በመጀመሪያ ዙር ነው ያለፈው።
Apr 01, 2026