ትልቁ የዘመኑ በሽታ ትክክል ብለሀል። ሀቁን ስነግርህ እኔ በ 4 አመት የምበልጣት እህት አለችኝ። 22 ትሆናለች። ውበትም ተሰጧታል። ግን ምን መሰለህ ችግሩ? ሰው የማርያምን ስም ጠርቶ የሚዋሽ አይመስላትም። ለገንዘብ ብሎ ሰው ጓደኛውን የሚክድ አይመስላትም ፣ የውሸት ለቅሶ ያለ አይመስላትም ። ንፁህነቷ ያስደነግጠኛል ወንድሜ። በእጅጉ ምን ያስፈራሃል ብትለኝ? የአሁን ዘመን ወንድ ልጅ። እኔ አስተዳደጌም ይሁን አላቅም ግን እህቶእቼን ስለማስብ ሴት አታልሎ ወደ አልጋ መውሰድ አልችልም ። ምናያቸው ወንዶችስ? ንግግራቸውን አይተሀል? ትዳርን ተወው ይቅር፤ ግን በትክክል ስለ ሴት ልጅ መፈጠር እና የሴት ልጅ ዋጋ ምን ያህል የገዘፈ መሆኑን ሚረዳ ወንድ አለ? ከትንሽ እስከ ትልቁ የሴትን ልጅ ጭን ማያስብ አለህ ብለህ ነው አሁን? ለሴቶች ብልግና+ድንግልና ማጣት ቁጥር 1 ተጠያቂ ማን ነው?
Mar 30, 2026