Serious question .... ወገንታት፡ በህጉ ዘርፍ ምን አይነት ችግር ቢፈታ እና ምን አይነት "ሲስተም" ቢለወጥ የህዝባችንን ችግር 1 ደረጃ ያቀላል ትላላችሁ? የ ህግ ተማሪዎች association አለን እና የህዝቡን ችግር እና ብሶት ብሰማ ደስ ይለኛል። " ይሄ ነገር አማሮኛል" የምትሉት ነገርም ካለ። አመሰግናለሁ
Mar 26, 2026የአስተዳደር ህግ ላይ ትልቅ ማሻሻያ ቢደረግ እላለሁ በተለይ በወረዳ፣ በቀበሌ፣ በክፍለ ከተማና በጤና ጣቢያዎች ያለው የመንግስት ሰራተኛ ለዜጎች ያለው ንቀት እና ባለቤት አልባ መሆን ህዝቡን ክፉኛ አማርሮታል ዜጋው በገቢ ግብሩ ደሞዝ ለሚከፍለው አካል እንደ ተመጽዋች መታየቱ ዛሬ ሂድ ነገ ና መባሉና በሰውነቱ ክብር ማጣቱ ትልቅ የህግ ጥሰት ነው ህገ-መንግስቱ የሰው ልጅ ክብር የማይደፈር ነው ቢልም በመሬት ጠብታ ላይ ግን ተግባራዊ ሲሆን አይታይም ለዜጋው ክብር የማይሰጥ፣ የሚያንገላታና የሚያቃልል ሰራተኛ በህግ ተጠያቂ የሚሆንበትና ዜጋው ካሳ የሚጠይቅበት ግልጽ የቅሬታና የቁጥጥር ሲስተም ቢዘረጋ የህዝቡን ምሬት 1 ደረጃ ሳይሆን 10 ደረጃ ያቀልለዋል
Mar 26, 2026