ቀልዱ ቀልድ ነው ይቺን በቁም ነገር ምክንያታዊ በኾነ መልኩ ምላሻችኹን አስቀምጡ ! ስለ7ቱ ሰዎች እንጂ እኔን መናገር ፈልጎ ነው እኔን ነው የተናገረው ብሎ ማሰብ ወይም ጠያቂውን ( እኔን ) መላሾቹንን እናንተን ፐርሰናሊ አታክ ለማድረክ መሞከር ድንቁርና ነው ! ደናቁርት ናቸው ሃገር ያጠፉት። በአንድ ጉባኤ ላይ 7 ሰዎች ተሰብስበዋል 1ደኛው ገንዘብን በጣም የሚወድ ፤ 2ተኛው ሐሜተኛ ፤ 3ተኛው መልካም የኾነውን የማይወድ ፤ 4ተኛው ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወድ ፤ 5ተኛው ተሳዳቢና ለአባቶቹ የማይታዘዝ ፤ 6ተኛው የማያመስገን እና እርቅን እሺ የማይል ሲኾኑ በመካከላቸው አንድ ሰው መጥቶ እናንተ የእፉኝት ልጆች ኹላችኹ ተስተካክላችኹ በአንድነት በደላችኹ ! እናንተ ወንበዴዎች እንግዲ ከሚመጣው እሳት እንደምን ትድኑ ይኾን ? በከንፈራችኹ ታመልኩኛላችኹ ልባችኹ ግን ከእኔ ርቋል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በማለት 7ቱን ሰዎች ዘልፏቸው ሄደ ! ! በዚኽ ጊዜ 7ተኛው ሰው ወደዚኽ ሰው በመሄድ እኔ እንደሌሎቹ አይደለኹም ! ኹላችንም አንድ አይደለንም ! ለይተኽ ተናገር በማለት ይኽን ሰው ዘለፈው ! ! " በ7ተኛ ላይ ያለው ሰው ምን አይነት ሰው ነው ? ? ከ7ቱስ ለእውነተኛ ንስሐ የማይበቃው የቱ ነው ?
Mar 24, 2026Nisiha megbat ena medan yeteleyaye neger nw...
Mar 24, 2026