JAHLEEL3956
#society
ብዙዎቻችኹ ኢንስታግራም ላይ ስትጠባበሱ እያየሁ ነው፤ እኔ ግን ይሄ ነገር እንዴት እንደሚሰራ ራሱ አላውቅም! ግን አንድ ጥያቄ አለኝ...ለመሆኑ ኢንስታግራም ላይ 'Filter' ሳይደረግ ቆንጆ መሆን በሕግ ያስቀጣል? አንድ ሰው ኢንስታግራም ላይ ፎቶ ተነስቶ ግን ማንም ሰው 'Like' ባያደርገው፣ ያ ሰውዬ በእውነት በሕይወት አለ ለማለት ይቻላል? ወይስ ኖሮም እንዳልኖረ ይቆጠራል? ያው ዴካርት 'አስባለሁ፣ ስለዚህ አለሁ' ብሎ ነበር፤ እናንተ 'ፎቶ እነሳለሁ፣ ስለዚህ አለሁ' እያላችሁን ነው ? ሌላው አንድ ሴት ቆንጆ ፎቶ ተነስታ፣ ፊልተር ተጠቅማ፣ ግን ማንም 'Like' ባያደርጋት... ያ ፎቶ በእውነት ቆንጆ ነው ሊባል ይችላል? ወይስ የሴት ልጅ ውበት የሚረጋገጠው በስልኩ 'Screen' ላይ በሚጫኑ ጣቶች ብዛት ብቻ ነው?
Mar 22, 20268 engagements