Anyone who explains this verse not being biased ቆላስይስ 2 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁰-²¹ ከዓለማዊ ከመጀመሪያ ትምህርት ርቃችሁ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ፥ ²² እንደ ሰው ሥርዓትና ትምህርት። አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ለሚሉት ትእዛዛት በዓለም እንደምትኖሩ ስለ ምን ትገዛላችሁ? እነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ ተወስነዋልና። ²³ ይህ እንደ ገዛ ፈቃድህ በማምለክና በትሕትና ሥጋንም በመጨቆን ጥበብ ያለው ይመስላል፥ ነገር ግን ሥጋ ያለ ልክ እንዳይጠግብ ለመከልከል ምንም አይጠቅምም።
Mar 22, 2026▶️፲፱.“ይህ እንደ ገዛ ፈቃድህ በማምለክና በትሕትና ሥጋንም በመጨቆን ጥበብ ያለው ይመስላል። ነገር ግን ሥጋ ያለ ልክ እንዳይጠግብ ለመከልከል ምንም አይጠቅምም" ይላል (ቈላ.2፥23)። ምን ማለት ነው? ✔️መልስ፦ የጥቅሱን ዋና ፍሬ ሐሳብ ከላይ ጀምረን ስናነበው እናስተውለዋለን። እየተነገረ ያለው ስለኦሪት ሕግ ማለፍ ነው። ኦሪት አትቅመስ እያለች ሥጋን ብትጨቁንም ነገር ግን በኦሪት የነፍስ ድኅነት አይገኝም ነበር። ኦሪት ብዙ መባልዕትን በመከልከል ሥጋ ያለ ልክ እንዳይጠግብ ብታደርግም ነገር ግን ይህ ሁሉ የነፍስ ድኅነትን አያስገኝም ነበር ማለት ነው። መምህር በትረማርያም አበባው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከቈላስይስ ክፍል ጥያቄና መልስ የተወሰደ
Mar 22, 2026