ሙስሊም ወዳጆቼ አላህ ሁለት ዒዶችን በአንድ ቀን አደረገልን። አል-ሐምዱ ሊላህ! እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ። አላህ ጾማችንን ይቀበል። ወንጀላችንን ምሮ ምህረቱን ይወፍቀን። ዒድ መጣልን። አዲስ ልብስ ያለን አዲሱን፤ የሌለን ደግሞ ያለንን አጥርተን ለብሰን የሃያሉ አላህን ስም ከፍ አድርገን እየጠራን፣ ተሰብስበን ሰግደን፣ ለወዳጅ ዘመዶቻችን መልካሙን እየተመኘን ቀኑን እናሳልፋለን። ከመልካሙም እንመገባለን። አንዳችንም ከፍቶን ልናሳልፈው አይገባምና በመረዳዳት፣ ያለው ለሌለው በማካፈል እናሳልፍ። የከፋችሁ ካላችሁ በውስጥ መስመር ዘይሩን። በገንዘብ ባናግዝ በሐሳብ፤ በሐሳቡ ቢከብደን በዱዐ አንረሳችሁም። አብሽሩ! እንኳን አደረሳችሁ ወዳጆቼ! 🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
Mar 19, 2026Ow that's sweet of you
Mar 19, 2026