መወለድ ጥቂት በጥቂት ማደግ መራብ መጠማት መድከም መዛል መተኛት መንቃት መውደቅ መነሳት መታመም መሞት መነሳት የመሳሰሉት የመለኮት ባሕርይ አይደሉም። መለኮት ተራበ ተጠማ ሞተ . . .ብሎ መናገር የማይገባ ብቻ ሳይኾን ክህደትም ጭምር ነው።( የመለኮት ባሕርይ አይለወጥምና) ሕማምና ሞት ፈፅሞ አያገኘውም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ ነውና በሥጋው ሞተ ስንል ነፍሱ ከመለኮቱ ያይደለ ከሥጋው ተለየች ፤ መለኮት ግን ከነፍሱም ከሥጋውም አልተለየም ከኹለቱም ተዋሕዶ አለ. . . .
Mar 19, 2026