Guys አሁን አንድ ጠንከር ያለ የመወያያ ሀሳብ ላነሳ ነዉ። አሁን ላይ ሀገራችንን ከዳር እስከዳር እያስቸገረ ያለዉ የኑሮ ዉድነት እና የነዳጅ እጥረት ምክንያቱ ብየ ማስበዉ ሀገራችን ሁሉንም ሸቀጥ ትምህርት ሙያ የአኗኗር ዘይቤ ወዘተ ቁሳቁስ የኛን ትተን የዉጭዉን መቀበላችን ነዉ። ከምንጠቀመዉ ቁሳቁስ (ስልክ ፒሲ መኪኖች ወዘተ)ጀሞሮ የምንማረዉ ትምህርት በጠቅላላ ከዉጭ የገባ ነዉ ይሄ ደግሞ በሂደት እሱ ላይ ጥገኛ እንድንሆን በማድረግ የገንዘባቸዉ ዋጋ ሲጨምር የመግዛት አቅማችን እየወረደ ከዉጭ የሚገቡ ዕቃወችን ቀርቶ ከጓሮአችን የሚመረተዉ የምግብ እህል ብርቅ እየሆነብን ነዉ። ነዳጅም እንደምታዩት የአረቦች ሰላም ሲታመስ የኛም ትራንስፖርት እየታመሰ ነዉ። ሳይንስና ቴክኖሎጅ ይቅርብን የሰዉ ሸቀጥ አጋባሽ አርጎናል።መፍትሄዉ የዉጭ ሀገር ጥገኝነትን መተዉ ነዉ የአኗኗር ዘይቤያችንን ትምህርታችን ግብርናችን ህክምናችን የመጓጓዣ ስልታችን ልብሳችን ቁሳችን ወዘተ ሁሉም ነገር ሀገር በቀል ማድረግ ነዉ።ያኔ ዶላር ቢጨምር ነዳጅ አምራች ሀገር ጦርነት ቢዋጋ ግድ አይሰጠንም ።ቀስ በቀስ እያልን የራሳችንን አኗኗር በሂደት እናስተካክላለን።ካልሆነ ግን ሁሌ ሌላ ሀገር ያመረተዉን በመግዛት እሱ ላይ ጥገኛ መሆን ከፍተኛ የዶላር ጥገኝነት እና ችግር ያመጣብናል። ሀሳብ ስጡበት 🙏🙏
Mar 17, 2026አቤት ጭንቅላት ታስብ የለ እንዴ እንዴት ነው ወደኃላ እንመለስ የምትለው ከቻልን የራሳችንን መስራት ነው ካልቻልን ደሞ አርፎ መጠቀም የዘመነ መሳፍንት ዘመን መመለስ ፈለክ ወይስ የጋርዮሽ ዘመን?
Mar 17, 2026