Ene mlachu....የምር ግን በህይወታቹ ደስተኞች ናቹ? ከልባቹ ነው የምትስቁት? ከልባቹ ነው የምትኖሩት? ውጪም ቤትም ያላቹ ማንነት አንድ ነው? እስኪ ከልባቹ መልሱልኝ ከልባቹ የምራቹን ደስተኞች ናችሁ?
Mar 13, 2026እኔ ደስተኛ አይደለኹም ! ምን አልባት ደስታ ከመብላት ከመጠጣት የራስን ምቾት ከመጠበቅ ወይም ከመሳሰሉት አንጻር የሚለካ ከኾነ የጎደለብኝ ነገር ስለማይኖር ደስተኛ ልኾን እችል ነበረ ነገር ግን ደስታ ማለት የእነዚኽ ነገሮች መሟላት ብቻ ሳይኾን የሀገርን የወገንን የቤተክርስቲያንን ጉዳዮችንም የሚያካትት ኾነና እነዚኽን ነገሮች ባስብኩ ቁጠር ልቤ ይደማል ለመደሰት ምክንያት አጣለኹ። መሽቶ በነጋ ቁጥር እግዚአብሔር ለዐዲስ ሕይወት እድል እየሰጠኝ በመኾኑ ደግሞ ደስ እያለኝ አዝናለው። የምስቀው ከልቤ አይደለም ! ከልቤ ከሳቅኩ ወደ አስር ዓመት ይኾነኛል ! አንድ አንድ የሚያስቁኝ ነገሮች የሉም ማለት አይደለም ግን ብስቅባቸውም ከሳቄ በኋላ የምድራችን እውነታ መልሶ ስለሚታወሰኝ ሳቄም ረጅም አይደለም ፈገግታ ብቻ ነው። የእውነት የምስቅበት ቀን ግን ይመጣል !
Mar 14, 2026