Guys ሰሞኑን አርሲ ዉስጥ ሰወች በሀይማኖታቸዉ ምክንያት ሲገደሉ ሰምተናል ደሞ እዛ ሀገር ይሄ ነገር ሲፈጠር በተደጋጋሚ ነዉ አሁን ላይ ደሞ በተለያየ ቦታ ያሉ ኦርቶዶክስ ሀበሻወች ንዴት ላይ ናቸዉ። ይሄም የመንግስት ችግር ነዉ መንግስት የዜጎቹን ደህንነት የመጠበቅና ወንጀለኞቹ ሲያመልጡ ተከታትሎ ይዞ ለፍርድ ማቅረብ አለበት። ግን አሁን ላይ ሀገራችን ሽፍትነት እና መሳሪያ ታጣቂነት ስለተለመደ ማንም ወንጀል ሰርቶ ይሰወራል ስለዚህ ለመንግስትም ሁኔታዉን መቆጣጠር ሊከብደዉ ይችላል። ግን ደሞ ነገርየዉ ሲደጋገም መንግስት ዝም ማለትን ሲመርጥ መንግስትን ራሱ እንድንጠራጠረዉ ያረጋል። ነገሩን ያረጉት መንግስት ህዝብን ለማጋጨት ብሎ ወይም ክርስቲያንን የሚጠሉ ነፍሰ ገዳይ ሙስሊሞች ይሆናሉ። ይሄ ሲሆን ደሞ ሌላ ቦታ ያሉ ሙስሊሞች አደባባይ ወተዉ ባይቃወሙም ቢያንስ በስሜታችሁ እንደምትቃወሙ እዚህ ላይ reply በማረግ ሀሳባቹን ግለፁ። ከዛ ሰሞኑን ደሞ ጎንደር ላይ አንድ ኡስታዝ ተገሏል በቀል ይሁን አይሁን አልተረጋገጠም በቀል ከሆነም እና ሰዉየዉ ንፁህ ሰዉ ከሆነ ትክክል ነዉ አልልም። የዚህ አይነት አዝማሚያ በጣም መጥፎ ነዉ ለሀገራችን በዚህ ጊዜ መፍትሄዉ ክርስቲያኑ በትዕግስት መንግስትን ፍትህ ነዉ መጠየቅ ያለበት ሙስሊሙም ድርጊቱን ተቃዉሞ መቆም አለበት። ግን እኔ ነገሩ ያስፈራኛል። የምፈራዉም ከሰዉ የተለየ ነፍስ ኖሮኝ ሞት ፈርቸ ሳይሆን ሰዉ አንድ ሆኖ ተፈጥሮ ሳለ በሀይማኖት ምክንያት መዋደድ አቅቶት የጎሪጥ እየተያየ ሲኖር ማነት ያሳዝናል። እዉነቱን ለመናገር መፍትሄዉ ሀይማኖት እና ብሄር የሚባል ነገር ማጥፋት ነዉ ከዛ ተዋደን አንድ ሆነን አርፈን እንኖራለን። አልያ ግን መንግስት ፈጣን እርምጃ መዉሰድ አለበት። Sorry ፅሁፉ ከረዘመ እስኪ ሀሳባቹን ስጡ 🙏
Mar 07, 2026Meftihew haymanot mibal negerin matafat new yalkew ere yemrkin new tikeldalek haymanoten kemitew bimot ayshalim ende bro eyasebk enji
Mar 08, 2026