Tiyake ayedelem be AAE lay letewawekut guwadegnaye melekam ledet lemalet new! this is for Mikopia :- Mikoye wendeme enkuwan aderesek ! Mekariye keleb amesegenalew ! bazenekubet seat yeneberek beretate ! be dekemeku seat yaberetahegne ! eyechegerek yeredahegne ! ENKUWAN TEWELEDEKELEGNE ! Zare 30 moltokal wey seregehen etebekalew ! ( AAE esun yemesele wendem endagegne mekeneyat selehonachehun amesegebalew ) Andebete re'tu defar le ewent yekome , negen ashagero eyetemelekete zaren beshenegela rasun yemayatalel hagerun yemiwed wendem ! bejegenoche ken bemeweledek yebelete destegna negne. . Rejem edeme Minilik.
Mar 02, 2026"ጻድቅ በጽድቁ ሲጠፋ ኃጥእም በክፋቱ እጅግ ዘመን ሲኖር ይኸን ኹሉ ከንቱ በኾነ ዘመኔ አየሁ" ። [መክብብ 7 ] ይኽንንም ስመለከት "ዐይኖችኽም ከሚያዩት የተነሳ እብድ ትኾናለኽ" [ ዘዳ 28 ] እንዲል ጨርቁን ያልጣለ እብድን ኾንኩ ። በዚኽም ደግሞ " ከመወለድ ቀንም የሞት ቀን ይሻላል " [ መክብብ 7 ] ስል የሞቴን ቀን ናፈቅኹ ። " ግፍንና ጠብን በከተማ ውስጥ አይቻለኹና " [ መዝ 54 ] " እናቴ መቃብር ትኾነኝ ዘንድ ማኅፀኗም ዘወትር ይዞኝ ያቆይ ዘንድ በማኅፀን ውስጥ አልገደለኝምና ድካምንና ጣርን አይ ዘንድ ዘመኔም በዕፍረት ታልቅ ዘንድ ስለምን ከማኅፀን ወጣኹ ? [ ኤር 20 ] ስል ራሴንም ጠየቅኹ ። ዳሩ ግን " ሴት ለመውለድ በደረሰች ጊዜ በሆዷም ያለ ፅንስ ለመወለድ በደረሰ ጊዜ ማኅፀኗን ለመከልከል እንዳትችል " [ 1መቃ 7 ] እናቴ እኔን በማኅፀኗ ሸሽጋ ታኖረኝ ዘንድ አልተቻላትምና " ለመወለድ ጊዜ አለው ለመሞትም ጊዜ አለው " [ መክብብ 3 ] በማለት በዘጠኝ ወር አልወለድም ያልኩ እኔን በአሥር ወር ከሦስት ቀን " ሰውነትኽን ለመከራ አዘጋጅ " [ ሲራ 2 ] በሚል የምጥ ሲቃ ወደ መከረኛዋ ዓለም እንደቀላቀለችኝ በማሰብ " ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ተደገፍኹ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ አንተ መሸሸጊያዬ ነኽ " [ መዝ 70 ] " የመድኀኒቴ አምላክ ሆይ አትተወኝ " [ መዝ 26 ] በሚል የተማጽኖ እንባ ከጠባቡ የእናቴ ማኅፀን ወደ ሰፊዋ የመከራ ምድር በ1988 ዓ.ም የካቲት ኻያ ሦስት ቀን በዓድዋ የድል በዓል ዕለትበእኔ ሚኪያስ ተወለድኹ ። በእድሜዬ ላይ እድሜን ስለጨመርኽልኝ " አቤቱ በፍፁም ልቤ አመሰግንሃለኹ " [ መዝ 9 ] " ግሩምና ድንቅ ኾኜ ተፈጥሬያለሁና አመሰግንሃለኹ "[ መዝ 138 ] " እንግዲኽ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለኹ " [ መዝ 62 ] " አቤቱ አምላኬ ለዘለዓለም አመሰግንሃለኹ " [ መዝ 29 ] " በቅዱሳንኽም ዘንድ መልካም ነውና ስምኽን ተስፋ አደርጋለኹ " [ መዝ 51 ] ክብር ምስጋና ይኹን ሰው አድርጎ ለፈጠረኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ! ክብር ምስጋና ይኹን ምልጃዋ ላልተለየኝ አምላኳን ለወለደች ለእመቤቴ ድንግል ማርያም ! ክብር ምስጋና ይኹን ሞገስ ለኾኝ መድኃኔዓለም ለተሰቀለበት ለቅዱስ ዕፀ መስቀል ! ክብር ምስጋና ይኹን ስማቸውን ለምጠራ ከፊት ከኋላ ከግራ ከቀኜ ለቆሙ ለመላእክት አለቆች ለሚካኤል ለገብርኤል ለሩፋኤል ለራጉኤል ! ክብር ምስጋና ይኹን ስሙን ስጠራው ፈጥኖ ለሚደርስልኝ ከሴት ከተወለዱ እንደሱ ያለ ላልተገኘ ጌታን ላጠመቀ ለአባቴ ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ! ክብር ምስጋና ይኹን ሃገሬን ከወራሪ ጦር ለጠበቀ በጸዐዳ ፈረሱ ተጭኖ ዘወትር ለሚጠብቀኝ ከጠላትም ከበባ ለሚታደገኝ ለክርስቶስ ወዳጅ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ! ክብር ምስጋና ይኹን ለእንጦስ ለመቃርስ ለተክለ ሃይማኖት ለገብረ መንፈስ ቅዱስ ፤ ለሀብተ ማርያም ለእስትንፋሰ ክርስቶስ ፤ ለአቢብ ለኪሮስ ስማቸው በልቤ ለተጻፈ ኹሉ ! አሜን። ፈቃድኽ ከኾነ በጎ የምሠራበትን እድሜ ጨምርልኝ ! ዓመት ዓመት አድርሰኝ 😁 ይቺን ዓመት ተወኝ ፤ ለንስሐ ሞት አብቃኝ ! ! ብሮ በድጋሜ አመሰግናለሁ ! !
Mar 02, 2026