Guys ኢትዮጲያ ዉስጥ ብዙ ጊዜ ሰወች አንድን ነገር ለማረግ ሀይማኖት ይፈቅዳል ወይም አይፈቅድም ብለዉ ራሳቸዉን ያስጨንቃሉ። ለምሳሌ ሴክስ ማረግ ፈልገዉ ወይም መጨፈር ዘፈን መስማት ፈልገዉ ፆም ላይ የፍስክ ምግብ መብላት ሲያምራቸዉ ሀይማኖት አይፈቅድም ብለዉ ፍላጎታቸዉን ያቅባሉ። I know religion ብዙ ነገር እኛን የሚጎዳን ነገር እንዳናረገዉ ሀጥያት ነዉ ብሎ ይገድበናል ግን ሁሉንም ነገር ሀይማኖት ስለከለከለዉ ብቻ ማድረግ ፈልገን መተዉ ያለብን አይመስለኝም ይሄ እኮ የአእምሮ ባርነት ነዉ ለሰዉ ደሞ ባርነት አይስማማዉም። እኛን እስካልጎዳንና በዙሪያችን ያሉትን ሰወች የማይጎዳ ከሆነ በነፃነት ማረግ አለብን። እኔም ከሀይማኖተኛ ቤተሰብ ነዉ የተወለድኩት ብዙ አመትም ሀይማኖተኛ ነበርኩ። ግን አሁን ሳስበዉ አንድ የሀይማኖት አባት ማረግ ያለብንን እና የሌለብንን ነገር ሊነግረን አይችልም በነፃነት መኖር አለብን.....እስኪ ሀሳብ ስጡ
Feb 21, 2026እንደ ኦርቶዶክስ አማኝ ክርስቶስ ነጻነትን ሰጥቶናል እንጂ አላስገደደንም። ከእሳትና ከውኃ መምረጥ ነጻነቱ የኛ ነው። እና ባርነት ውስጥ አይደለንም፤ ነጻነት ውስጥ እንጂ። አንድ ነገር ይጉዳኽ አይጉዳኽ ደግሞ አባትኽ መክሮ እንደሚያሳድግ ሁሉ ቤተክርስቲያን መክራ አስተምራ ታሳድገናለች። ያ ደግሞ ለውሳኔ እንዲረዳን ነው።
Feb 21, 2026