SPBD46.5
#business
አስቸኮይ ነው ፤ አስቸኮይ ነው ሰላም ጤና ይስጥልኝ የዚህ ግሩፕ አባላት! 👋✨ አንድ የሥራ ዕድል አግኝቼ የዋጋ ተመን (Rate) ለማውጣት የእናንተን ልምድና ምክር ፈልጌ ነበር። ✍️📖 የሥራው ሁኔታ፦ - የገጽ ብዛት፦ 223 ገጽ 📄 - የመጽሐፉ ዓይነት፦ መንፈሳዊ (Spiritual Book) ⛪️✨ - የሥራው ዓይነት፦ ይዘቱ በጣም የተበታተነ በመሆኑ፣ ሃሳቡን ከመሰረት ማደራጀት፣ ቅደም ተከተሉን ማስተካከል እና መጽሐፉን ሕያው የማድረግ (Developmental Editing/Structuring) ሥራ ነው። ይህንን ሥራ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ሰርቶ ለማጠናቀቅ፣ አሁን ባለው የገበያ ሁኔታ ግለሰቦች ወይም ባለሙያዎች በአማካኝ ምን ያህል ክፍያ ይጠይቃሉ? 💰🇪🇹 ልምድ ያላችሁ ወዳጆቼ ብታካፍሉኝ ትልቅ እርዳታ ይሆንልኛል። ለምታደርጉልኝ ትብብር በቅድሚያ አመሰግናለሁ! 🙏 የክብር ሰላምታዬ ይድረሳችሁ። 🕊️🌟
Feb 19, 20264 engagements