ሰላም ንስሐ ለመግባት ፈልጌ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ። እና እንዴት እንደምናዘዝ መናዘዝ ያለብኝን የኃጢአት ዝርዝር እና ጠቅላላ ነገር ብትነግሩኝ አመሠግናለሁ
Feb 07, 2026#መቼ_ልሞት_ይሆን?😢😢😢 #ሳልሞት_እንዴትስ_ብዬ_ልናዘዝ? የሰዎች ኃጢአት ከ10ሩ ቃላተ ኦሪትና እና ከ6ቱ ቃላተ ወንጌል አይወጣም፡፡ 1 .- ፈጣሪዬን ክጃለሁ፡፡ - በጠንቋይና በደብተራ አምኜ ሰግጃለሁ፡፡ - በወንዝ በዛፍ… አምልኬያለሁ፡፡ - በስልጣኔ ፣ በገንዘቤ፣ በጉልበቴ፣ በሰው፣ በመልኬ ተመክቻለሁ፡፡ - ኮኮብ ቆጣሪ / አስትሮሎጂ፣ አውደነገስት/ ሆኛለሁ፡፡ 2.- በእግዚእብሔር ስም በከንቱ ጠርቻለሁ፡፡ - በእግዚአብሔር ስም በሃሰት መስክሬያለሁ፡፡ - በጸሎት፣ በቅዳሴ ግዜ አውርቻለሁ፡፡ - የእግዚአብሔርን ስም የለቦታው ጠርቻለሁ፡፡ - ድንግል ማርያምን በከንቱ ጠርቻለሁ፡፡/ በሆነ ባልሆነው መርያምን… ማርያምን አይባልም/ - በስሙ ቃልኪዳን ገብቼ አፍርሻለሁ፡፡ - ሰውን በሃሰት አስምያለሁ፡፡ 3. -ሰንበትን ሽሬያለሁ፡፡ - በሰንበት ቤተክርስቲያን አልሄድኩም፡፡ - በሰንበት ተራክቦ ፈጸምኩ፡፡ - በሰንበት መልካም ስራ አልሰራሁም፡፡ 4. - አባት እናቴን ዋሸሁ፣ አታለልኩ፣ ሰደብኩ፡፡ - አባት አናቴን አላከበርኩም፣ አረዳሁም፣ ንቄያለሁ፡፡ - አባትና እናቴን አሳዝኛለሁ፡፡ 5.- ሰው ገደልኩ ፣ አስገደልኩ፡፡ - ጽንስን አስወረድኩ፡፡ - ሰውን አማሁ፡፡ - እርቅን አምቢ አልኩ፡፡ -በኃጢአት ነፍስን ገደልኩ፡፡ 6.- ዝሙትን ፈጸምኩ፡፡ - ግብረ ሰዶም ፈጸምኩ፡፤ - አራስ ሴት ተራክቤአለሁ፡፡ - ሴትን በወር አበባዋ ግዜ ተገናኘሁ፡፡ - በህልሜ ተራክቦ ፈጸምኩ፡፡/ ያሰብከው ሰው ጋር ከሆነ/ - ሌላ እምነት ካለው ሰው ጋር ተራክቦ ፈጸምኩ፡፡ 7.- የሰውን ንብረት ሰረቅሁ፡፡ - ጉቦ ሰጠሁ፣ ጉቦ ተቀበልኩ፡፡ - የሰው አደራ በልቻለሁ፡፡ - ከሌባ ጋር ገንዘብ ተካፈልኩ፡፡ - አጭበረበርኩ፡፡ - ተበድሬ አልመለስኩም፡፡ - የእግዚአብሔርን ገንዘብ ወስጃለሁ ፡፡/ አስራቱን/ - የልጅ ፣ የድሃ ጉልበት በዘበዝኩ፡፡ 8.- በሃሰት መሰከርኩ፡፡ -ባለቤቴን ፣ ሰውን ወሸሁ፡፡ - ዋሽቼ አተረፍኩ፣ ተሸለምኩ… - በፈጣሪ ስም በውሸት ማልኩ፡፡ 9. የጓድኛየን ንብረት፣ ሚስት፣ ባል፣ እውቀት.. ተመኘሁ፡፡ -ስምና ዝና ተመኘሁ፡፡ - ያየሁትን ወንድ፣ ሴት ተመኘሁ፡፡ 10.- ሰውን ጠልቻለሁ፡፡ - ሰውን በዘር ለይቼ ጠልቻለሁ፡፡/ አማራ፣ ትግሬ ፣ ኦሮሞ በማለት/ -ቀናተኛ ነኝ፡፡ - እኔ የምጠላውን ለሰው ሰጥቻለሁ፡፡ -ድሃ ጠልቻለሁ፡፡ - ሰው የሚጎዳ ስራና ሃሳብ ሰራሁ፡፡ - በበሽተኛ ሰው አሾፍኩ፡፡ 11.- ሰውን በከንቱ ተቆጣሁ፡፡ - ስሳደብ ኖርኩ፡፡ -ቧልተኛ ነኝ፡፡ 12.- ሴትን / ወንድን አይቼ ልቤ ከጀለ፡፡ -የዝሙት ነገርን ተናገርኩ፡፡ 13.- በትዳሬ አልጸናሁም፡፤ -ትዳሬን ፈታሁ፡፡ - የተፈታችውን አገባሁ፡፡ -ሱሰኛ፣ ፌዘኛ፣ ሴሰኛ ነኝ፡፡ 14.- በሃሰት ስምል ኖርኩ፡፡ -በመላእክት፣ በቅዱሳን፣ በእመቤታችን… ስም ማልኩ፡፡ 15.- ሰውን ተበቀልኩ፡፡ -ሲሰድቡኝ ሰደብኩ፡፡ 16.- ጠላቴን ጠላሁ፡፡ -ሰውን በዘር ጠላሁ፡፡ -1.-ለተራበ አላበላሁም፡፡ 2. -ለተጠማ አላጠጣሁም፡፡ 3.- እንግዳ አልተቀበልኩም፡፡ 4.- ለታረዘ አላለበስኩም፡፡ 5.- የታመመን አልጠየኩም፡፡ 6.- የታሰረን አልጠየኩም፡፡ በተጨማሪም፡- - ኩል ተኳልኩ - ከንፈሬን ፣ ፌቴን ምናምቴ ተቀባሁ፡፡ - ጸጉሬን ተቀለምኩ፡፡ - ሌላ ጸጉር ቀጠልኩ፡፡ -ሱሪ ለበስኩ፡፡ - ራሴን የሚያራቁት/ ዝሙት የሚያነሳሳ/ ልብስ ለበስኩ፡፡ - ጫት በላሁ፡፡ - ሲጋራ ጠጣሁ፡፡ - ሃሺሽ ጠጣሁ፡፡ - ፋሺን ተከታይ ነኝ፡፡ - ቡጭቅ ልብስ አለኝ፡፡ በተለይ በአሁኑ ሰዓት የኃጢአት መንገዱ ብዙ ነው፡፡ በንስሐ አባት በተደጋጋሚ ንስሐ ተሰጥቶ የኃጢአት እከክ ከተራገፈ ቡሃላ መቁረብ ነው፡፡ በማንኛውም የእድሜ ክልል የሚገኝ ክርስቲያን መቁረብ አለበት፡፡ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው፡፡ እንደ ዘመነ ኖኅ ሰዎች በዚህ ጊዜ እንዲህ አደርጋለሁ ማለት በራስ ላይ መፍረድ ነው፡፡ዘመኑ የቅዝፈት ነው፡፡ ወጣቱ ስጋውን እና ደሙን ተቀብሎ መቀመጥ አለበት፡፡ተዘጋጅተህ ጠብቅ፡፡ - ብዙዎቹን ይህንን ጽሁፍ እንዳያነቡ ይጋርዳቸዋል፡፡ ንስሐ እና ቁርባን ሰይጣን አይወድም፡፡ወገናችንን በዘፈን እና በመጠጥ እያሳሳቀ እየወሰደ ነው፡፡ ግዜው አልቋል፣ግዜው አልቋል እግዚአብሔር ለንስሃ ሞት ያብቃን🙏🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር አሜን ይቆየን!!!
Feb 08, 2026