ሰላም ቤተሰብ😊 1 ጥያቄ: ስራ አያፀድቅም በፀጋው ብቻ ነው የሚል ት/ት አለ የኔ ጥያቄ ጌታ በመጨረሻው ሰዓት የሚናገረው ነገር ከስራ ጋር ነው የሚገናኘው "ብራብ አላበላችሁኝም፣ብጠማ...፣ብታሰር አልጠየቃችሁኝም...እና ሌላ ቦታ ላይ “... ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ አለው።” — ማቴዎስ 19፥17 እስቲ አብራሩልኝ just ጥያቄ ነው።ለማወቅ።
Jan 30, 2026ጥሩ ጥያቄ ነው። በጸጋ ነው አንድ ሰው ሊድን የሚችለው 100% ጥያቄ የለውም፣ የትኛው ጽድህ ነው ደሞ ለመዳንህ መዋጣት የሚችለው? መልዓክቶች እንኳን በእግዚአብሄር ፊት እንከን አይጠፋባቸውም ኢሳይያስ 64:6 ሁላችን እንደ ረከሰ ሰው ሆነናል፤ የጽድቅ ሥራችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችን እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ ኀጢአታችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎናል። የጽድቅ ሥራችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው ያለው ነብዩ ኢሳያስ ነው፣ እንግዲህ ከኢሳያስ የተሻለ ጽድቅ ካለህ አሳየኝ። እና ወደ ጥያቄህ ስገባ፣ የሎሚ ዛፍ አናናስ ሊያፈራ ይችላል? መልስ አይችልም ነው። ማቴዎስ 7፡17 እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል። 18መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም። ይሄን ያዝልኝ 2 ቆሮንቶስ 5:17-21 ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው አየህ? በክርስቶስ እውነተኛ የሚያድን እምነት ያለው በእግዚአብሄር ሉዓላዊ ጸጋ አዲስ ፍጥረት ይሆናል፣ በመንፈስ ቅዱስ ልቡ ይቀየራል። እና ማንም እየመጣ እኔ አምኜ ነበር ሊል ይችላል፣ ግን ሰው የእግዚአብሄርን ትእዛዛት ሊጠብቅ የሚችለው ዳግም ከእግዚአብሄር ከተወለደ ብቻና ብቻ ነው። እግዚአብሄርን ምንም ብትሞክር፣ ተራራ ላይ ወተህ ብታድር ባለህ ደካማና ሃጥያተኛ ስጋ ልትታዘዝና ደስ ልታሰኝ አትችልም። ዕብራውያን 11:6 ደግሞም ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሠኘት አይቻልም፤ ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ሁሉ እግዚአብሔር መኖሩንና ከልብ ለሚሹትም ዋጋ እንደሚሰጥ ማመን አለበት። የሚያምን ሰው ስላመነ እና በመንፈስቅዱስ ስለተለወጠ እግዚአብሄርን ይታዘዛል። መታዘዙም ከእግዚአብሄር የመጣ ጸጋ ነው። አምኛለሁ ብሎ የማይታዘዝ የምር አላመነም ነው ነጥቡ።
Jan 30, 2026