ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ካለፈው ዓመት ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ6ወራት ውስጥ ከሰኔ 1 እስከ ታኅሳስ 1ድረስ ብቻ የትዳር ፍቺ 54 በመቶ መጨመሩ ተገልጿል ! 5805 ጥንዶች ተፋተዋል ! ! በዚኽ ፍቺ ምክንያት 668 ሕፃናት ከአንደኛው ወላጃቸው ጋር ብቻ እንዲኖሩ ተገደዋል ! ! ይኽ አስደንጋጭ የኾነ መረጃ ከወጣ በኋላ ለትዳር መፋታት ምክንያት ናቸው ብለው ሰዎች ካነሷቸው ነጥቦች መሐል የተወሰነውን አስቀምጥላችኋለው :- እናንተ የራሳችኹን ግምት አስቀምጡልኝ ! ተምሬአለው ሠልጥኛለው ሃይማኖት አለኝ የሚል ትውልድ ትዳርን ያቀለለበት ምክንያት ምንድነው ? አንተ ለሴት ልጅኽ የምትመኘውን ባል አይነት ነኽ ? አንቺ ለወንድ ልጅሽ የምትመኛትን አይነት ሚስትስ ነሽ ? ቆም ብለን ማሰብ እንዳንጀምር አእምሯችን በምን ተጋረደ ? ሕይወት የሚገኝበትን ቃል ከመነጋገር ይልቅ ለቧልት እና ለፌዝ እንዴት ልንተጋ ቻልን ?
Jan 29, 2026Am sorry to say this, ግን JAHLEEL ምትባለው ሰው ጤንነትህ ደና ነው? BTW ትንሽ ስልጣኔ ጥሩ ነው እሺ ስታስጠላ🤦♀️
Feb 01, 2026