Edemeyachu ke 19 amet blay yehonachu ena bezu ngern experienced yadergachu sewoch bicha lelochachu elfu Le andit 19 amet wetat set mn ayinet meker yinorachual lmsale wdeene edeme betmelsu metastekallut nger wezte Bekedemiya selken lbachu amesegenalew
Jan 29, 20261. ጊዜሽን በአግባቡ ተጠቀሚ ፣ አልባሌ ቦታ ከመዋል ወይም ዝምብሎ Social media ላይ ከመባከን ተቆጠቢ። 2. ከትምህርትሽ ጎን ለጎን መፅሃፍቶችን ማንበብ ልመጂ። - መፅሃፍትን ማንበብ ምን ያህል ጥቅም እንዳለው ብዙሃኑ የተረዳው አይመስለኝም ፣ ነገር ግን አንቺ ከአሁኑ ማንበብ ብትጀምሪ ታተርፊበታለሽ። "Reading has tons of benefits not only for knowledge , but for brain power, increasing confidence , improving vocabulary, speaking skill, and etc.." You can search the details on Google - ሌላው ወደፊት የራስሽን ስራ መስራት የምትፈልጊ ከሆነ የBusiness መፅሃፎችን ማንበብ ፣ ፍላጎትሽ ሌላም ከሆነ Google አድረገሽ አልያም telegram ላይ ብዙ የመፅሃፍት ቻናሎች አሉ ፣ እነሱ ላይ የሚመችሽን መርጠሽ አንብቢ። If u want those channels I can send you the link, just reply for this response, and I'll forward them. - በተቻለ መጠን hardcopy ገዝተሽ ፣ መፅሃፉ ገቢያ ላይ ከሌለ ደግሞ print አስደረገሽም ቢሆን አንብቢ እንጂ softcopy አትጠቀሚ (ይህ የግል ምክሬ ነው ፣ ሌላ ሰው በsoftcopy አንብቢ ሊልሽ ይችላል) 3. እንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪ ፣ የምትችይ ከሆነም በየጊዜው ለማሻሻል ሞክሪ - ኮምፒውተር እና ስልክ ካለሽ ፣ ከራስሽ አልፎ ለሌሎች ሰዎች ሊጠቅም የሚችለው አንዱ ነገር ቢኖር እንግሊዝኛ መማር ነው ፣ በተጨማሪም ማንኛውንም አይነት ሙያ ከኢንተርኔት በራስሽ እንድትማሪ በእጅጉ ያግዝሻል። 4. ሙያ ተማሪ - ከላይ እንደጠቀስኩት በቂ የእንግሊዝኛ ካካበትሽ በኋላ ፣ ቀጣይ ማድረግ ያለብሽ ነገር ሙያ መማር ነው ፣ ታዲያ ይህ ሙያ ግን የግዴታ የሰዎችን ችግር የሚፈታ መሆን ይኖርበታል። ለምሣሌ በአሁኑ ጊዜ ገበያ ላይ ተፈላጊ የሚባሉት የonline ሙያዎች እነዚህ ናቸው👇 - Video Editing - Customer Service - Virtual Assitant - Web development - Copywriter - Social media management - Content creation .... ወዘተ ሌሎችም አሉ ፣ ኢንተርኔት ላይ search አድርጊ 5. በመንፈሳዊ ህይወት መበርታት - ከፈጣሪ ጋር ያለሽን ቀረቤታ መጨመር ፣ ክርስቲያን ከሆንሽ መፅሐፍ ቅዱስ ማንበብ ፣ መፀለይ ፣ ከሌሎች ጋር ያለሽን ህብረት ማጠናከር ( ማለትም ቤተክርስቲያን መሄድ)። መልካም ሁሉ ይግጠምሽ🙏 በርቺ!
Jan 29, 2026