ሰላም እንዴት ናቹልኝ ??? ሴት ነኝ 22 አመቴ ነው ቆይ ግን በዚ ሰአት ምንም ብር የሌለው አይዞሽ ባይ የሌለው ግራ ግብት ያለው ሰው አለ እንዲ ስሰቃይ በዚች አለም ላይ ብቻዬን የተፈጠርኩ እስኪመስለኝ ብቸኝነት ያጠቃኛል ......... ወደፊት ምንም አይታየኝም ተስፉ ሚባል ነገር አይታየኝም ነጋ መጨነቅ መሸ መጨነቅ ነው ሁሌ ጸልያለው ስራ እሰራለው ግን ከቤት ኪራይ እና ከአንዳንድ ነገር አያልፍም አንዳንዴ ለምን በቃ ወደ እናቴ ጋ ተመልሼ አልኖርም እላለው የእናት ቤት comfort zone እንደሆነ ግልፅ ነው ግን እስከመቼ ????? እራሴን ችዬ እናቴን ለማገዝ ነው i know ለራሷ አታንስም ጥሩ ላይ ነች ግን አድሜ ይገፉል ጉልበት ያልቃል ለወደፊቷ እኔ ጠንክሬ ጥሩ ደረጃ ላይ መድረስ አለብኝ ግን በቃ ግራ ገብቶኛል
Jan 28, 2026አይዞሽ ታለም ባይሆን ይህ የጻፍሽው ጽሑፍ ከኛ ይልቅ ለእናትሽ ብታማክሪያት በትንሹ ከዱዐ/ጸሎት ጀምራ መፍትሔ እስከማስቀመጥ ትተባበርሻለች። አንዳንዴ ችግሩ ከኛ መሆኑን እንረሳለን እንጂ ማንን በየትኛው ሰዓት ማማከር እንዳለብን ብናውቅ ብዙ ባልተጎዳን ነበር። እናትሽ ጋር ሄደሽ ምክሯን ጠይቂ። "ለላም ቀንዷ አይከብዳትም።"
Jan 28, 2026