#Day_1 ሰዎች እንዴት ናቹ ሰሞኑን ከ 50 አመት በላይ የሆነው መፀሀፍ ከ አንድ ሽማግሌ አግንቸ ነበር ያስገረመኝ የመፀሀፉ እድሜ ሳይሆን የያዘው እውቀትና የአዛውንቱ ማስፈራሪያ ነበር አንዴ ከገባህበት አትወጣም ይጠራሀል ነበር ያለኝ መፀሀፉ አውደ ነገስት ይባላል ስለ ኮከብ ቆጠራና የተለያዩ ድግምቶች ያለበት ነው እኔ የ Computer Science ተማሪ ነኝ ወደ app ልቀይረው አስቤ ነበር ግን እንደተረዳሁት ከሆነ ኮከብ አቆጣጠሩ በሚቆጠርለት ሰው ስም እና በ እናት ስም ነው ሚቆጠረው እና እያይዳንዱ ፊደል የራሱ ቁጥር አለው ምን ለማለት ነው ወደ app ለመቀየር ፈተና የሆነው ነገር ለምሳሌ ሀይሌ ሚባል ሰው ልቁጠር ብል "ሀ" ብቻ የተለያየ ስለሆነ ይህን መረዳት ይከብዳል ሌላው ነገር ደሞ ጥቁር አስማቶች ተካተውበታል ሰውን እንዴት መጉዳት እንዳለብን የሚያስተምሩ ለምሳሌ መስተፋቅር,ማሳመም,መግደል የመሳሰሉት አስፈሪ ድግምቶች ሲኖሩ የገንዘብ የእድል የአደጋ መከላከያም ድግምቶች አካቶ ይዟል የኔ ጥያቄ ይሄን የጥንቆላ መፅሀፍ 400 ብር ልሸጠው ተስማምቸ ነበር ግን የሚያደርሰውን ሳስብ ከበደኝ እንዳላቃጥለው ታሪክ ነው ምን ይሻለኛል
Jan 26, 2026አቃጥለው፣ ምንም ለሰው ልጅ ም ሆነ ለወገንህ የሚጠቅም እውቀት የለውም፣ ከሺህ አመታት በፊት በጠንቋዮች የተጻፈ የማታለያ ቢዝነስ የሚሰራበት መፅሀፍ ነው፣ ለማስታወስ ደግሞ በየቦታው የተታለሉ ሰዎች የሚገዙት መፅሀፍ ነው ብርቅዬ አርገህ አታስበው፣ መፅሀፈ ሄኖክ እንደሚያስረዳው የወደቁት መላእክት ለሰው ልጆች ካስተማሩት ራሳቸው የሰው ልጆችን corrupt ከሚያደርጉ ነገሮች አንዱ ይህ መፅሀፍ ነው የሚገርመው ነገር ለዚህ ሁሉ ሺህ አመታት ሰው ለልጁ የሚያጠፋውን የሚጎዳውን እሱንም የልጅ ልጁንም የሚጎዳውን ነገር እያወረሰ እዚህ እስከ እኛ ትውልድ ድረስ መድረሱ ነው Computer Science የተማርከው ለራስህም ለወገንህም ጥቅም ለመስጠት ነው እንጂ የሚጎዳ ነገር ስታስቀምጥ አይደለም፣ help your fellow humans bro፣ cut ties with this a thousands year old nonsense.
Jan 26, 2026