ሰላም ቤተሰቦች ኦርቶዶክሶች በቀናነት መልሱልኝ እባካችሁ ክርስትና የምንነሳበት ምክንያት ምንድነው? ለቀና መልሳችሁ በጣም አመሰግናለሁ
Jan 24, 20261. #ምሥጢረ ጥምቀት ይህ ሥርዐት የሚፈጸመው ላመነ ሰው ብቻ ነው፡፡ ማር.፲፮፡፲፮ (16፥16) ሙሉ ሥርዓቱ የሚፈጸምበት “መጽሐፈ ክርስትና”የተባለ መጽሐፍ አለው። #ለመጠመቅ ዕድሜ ምን ያህል መሆን አለበት ? ሀ/ ከአውነተኛይቱ እምነት ከተዋሕዶ ውጪ ለሆነ ሰው መጀመሪያ የቤተከርስቲያኒቱን እምነትና ሥርዓት መማር አለበት። ማመንም አለበት። “ባመነም ጊዜም የሚስጠውን ቀኖና ፈጽሞ ይጠመቃል" ያመነ የተጠመቀ ይድናል ፡ ማር.፲፮፡፲፮ (16፥16) ለ/ ከከርስቲያኖች /ከተዋሕዶ/ አማኝ ከከርስቶስ ወገን ለሆኑ ቤተከርስቲያናችን ሥርዓትን ሠርታለች። ይኸውም ወንዶች በተወለዱ በ4ዐ ቀናቸው ሴቶች ደግሞ በ8ዐ ቀናቸው ይጠመቁ ዘንድ። ይህም ምሳሌ አለው፡- አዳም በተፈጠረ በ4ዐ ቀኑ ሔዋን ደግሞ በ8ዐ ቀኗ ወደ ገነት መግባታቸው ኩፉሌ ፬ ; ፱ (4፥9) ሴት ልጅ ወንድ ስትወልድና ሴት ስትወልድ የመንጻት ልማዷ ወንድ ከወለደች 40 ቀን ሴት ከወለደች 8ዐ ቀን ስለነበር። ዘሌ 12 በነዚህ ምሳሌዎች ቤተከርስቲናችን ለክርስቲያን ልጆች አንዲህ ሥርዓትን ሠራች። ሕፃናት ሲጠመቁ የከርሰትና አባት ወይም የከርስትና እናት ይደረጋል። ይሀም ሕፃናቱን የሃይማኖት ትምህርት ያስተምሩ ዘንድ ነው። ሕፃንም ይሁን ትልቅ ሰው በሚጠመቁበት ጊዜ ሦስት ጊዜ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ከሰገዱ በኋላ ይጠመቃሉ። ከዚያም ሥርዓተ ቅዳሴው ተፈጽሞ ሥጋውንና ደሙን ይቀበላል። #ጥምቀት የሚደረገው በውኃ ብቻ ነው። ተጠማቂው ሦሰት ጊዜ በውኃ ውስጥ ብቅ ጥልቅ ይደረጋል ወይም ካህኑ በላዩ ያፈስበታል። ምሳሌነቱ የጌታችን ሞቱን መቀበሩንና ከሞት መነሣቱን የሚያስረዳን ነው። ከተጠመቀ በኋላ ማዕተብ በአንገቱ ይታስርልታል። ይህም ጌታን በጦር ሲወጉት ከጎኑ የፈሰሰው የደሙና የውኃው ምሳሌ ነው። ጥምቀቱ ከመንፈስ ቅዱስ መወለድ ስለሆነ አንድ ጊዜ ብቻ ነው አይደገምም። ሁለት ጥምቀት የለም ሃይማኖት አንዲት ብቻ ስለሆነች ጥምቀትም አንዲት ናት። ኤፌ ፬፡፭ (4፡5) ስለዚህ በሌላ እምነት የነበረ ሰው ሁሉ ወደ ኦርቶዶክሰ ተዋሕዶ አንዲት ሃይማኖት ሲመጣ ጥምቀት ይፈጸምለታል። #ማዕተብ (በአንገት የሚታሰሩ ከሮች) ማዕተብ የሚለው “ዐተበ” ባረከ ከሚል የግእዝ ቃል የወጣ ነው። ማዕተብ ስንል የተባረከ ይሆናል። በአንገታችን የምናሰራቸው ክሮች ተባርከው ስለሆነ በዚሁ ማዕተብ ተብለው ይጠራሉ። #ነጭና ቀይ ማዕተብ ነጭና ቀይ ክር በከርሰትና ጊዜ የሚታሰር ሲሆን ትርጉሙም ጥምቀት የጌታችንን ሞትና ትንሣሌ የምናሰብበት ሰለሆነች ይኸውም ወደ ውኃው መጥለቅ እንደ መቃብር፤ ከውኃው መውጣት እንደትንሣኤ ነውና። “…ከኢየሱስ ከርስቶስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደተጠመቅን አታውቁምን? “ ከብር ይግባውና ጌታቸችን በቀራንዮ በመስቀል በተሰቀለና ሞትን በቀመሰ ጊዜ ቅዱሰ ዮሐንስ እንደጻፈው ከጭፍሮቹ አንዱ ይላል ለንጊኖስ ይባላል በጦር የጌታችንን ጎኑን ወጋው በዚህ ጊዜ ደምና ውኃ ፈሰሰ። “፩ዱ እምሐራ ረገዞ ገቦሁ ዘየማን በኲናት ወሶቤ ወጽእ አምኔሁ ደም ወማይ “ከጭፍሮቹ አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው ያንጊዜ ደምና ውኃ ወጣ የሐ ፲፱;፴፬ (19:34) ከዚህም ምሥጢር የተነሣ በጥምቀት ጊዜ የሚታስረው ቀይና ነጭ ክር የደሙና የውኃው ምሳሌ ነው። #ጥቁር ማዕተብ ጥቁር ማዕተብ ደግሞ በጥምቀት ያገኘናት ሃይማኖታችን በዚህ ዓለም ስንኖር ፈተናና መከራ አንዳለባት የሚያሳይ ነው፡፡ በዚህ ሃይማኖት በወርቅ ትመሰላለች ወርቅ ወርቅነቱ የሚታወቀው በእሳት ተፈትኖ ነው። ሃይማኖትም ጽኑ መከራዎችና ፈተናዎችን በማለፍ ነው። “በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ” ዮሐ ፲፮፡፴፫ (16፡33) #ክታብ ከዚህ በተጨማሪ በሕግ መጽሐፍ አንደተጻፈ አንዲህ ሲል “አኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ ለልጆችህም አስተምረው በቤትህም ስትቀመጥ በመንገድም ስትሄድ ስትተኛም ስትነሣም ተጫወተው፡፡ በአጅሀም ምልከት አድርገህ አስረው በዓይኖችህም መካከል እንደ ከታብ ይሁንልህ። በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው፡፡ “ዘዳግ 6:6-9 በሚለው መሠረት ብዙ ከርሰቲያኖች ክታብን በአንገታቸው ያደርጋሉ።ክታብ ማለት ጽሑፍ ሲሆን ይህም የእግዚአብሔር ቃል ነው።በተለይ “ትምህርተ ኅቡዓት” በአንገት ይታስራል። ትምህርተ ኅቡዓት ከሰባቱ ኪዳናት አንዱ ሲሆን ጌታችን ይህን አሰተምሯቸዋል ሰይጣን በዚህ አሯአል ሰለዚህም በተለይ ለልጆች በአንገታቸው ያስሩላቸዋል። ከአግዚአብሔር ቃል ውጪ የሆነ ሌላ አሸንከታብ ሁሉ የተከለከለ ነው። ኃጢያትም ጭምር ነው።
Jan 27, 2026