ጥያቄ ለሴቶች እህቶች ያገባችሁት ሰው ከእናንተ በፊት ልጅ ቢኖረው እና ቢደብቃችሁ ምን ይሰማቹሃል? ማለት ግን ምንም ችግር የለበትም፣ በጣም ነው የሚወደኝ፣ ይንከባከበኛል፣ በጣም ጥሩ ባል ነው፣ ሲበዛ ታማኝ ነው፣ በፊት ከነበሩት ፍቅረኞች ጋር አሁን ላይ ምንም ግንኙነትም ሆነ ፍላጎት ወይ ፀፀት፣ ትዝታ የለበትም፣ ስማቸውን ሁላ አያነሳም። እንዳልነበሩ ረስቷቸዋል፣ ልጁም ቢሆን ህይወቱ ውስጥ ቦታ የለውም፣ ከመጋባታችን በፊት ነው ያደገው፣ የልጁ እናቱ ከልክላውም ነበር። ምንም የእኛ ትዳር እና ህይወት ላይ የሚያሳድረው ትፅእኖ የለም። እሱ ነግሮኝ ሳይሆን በቅርቡ ከሰው ነው ያወኩት እና ምንም ሊሰማኝ አልቻለም፣ ምን ብዬ ትርጉም እንደምሰጠውም አልገባኝም። እናንተ ብትሆኑ ምን ይሰማቹሃል? እንደ ክህደት ታዩታላቹ? ወይ እንደ ሰብአዊ መብት ጥሰት? የብዙዎቻችሁን ሃሳብ ያስፈልገኛል። ከሱም በትጨማሪ ደግሞ እንደ ክህደት የምታዩትም ካላችሁ ለእናንተ ያለውን ክብደት እና ትርጉም በስፋት ብታብራሩልኝም ደስ ይለኛል። I also accept answers in English as well.
Jan 17, 2026ይሄን ያህል ነገር ለምን እንደደበቀሽ እራሱን ብትጠይቂው ነው ሚሻልሽ ጥሩ ባል ከሆነ እና አንቺን ምንም መጥፎ ነገር ካልተሰማሽ ለምን የሰውን approval ትጠይቂያለሽ? ሰው እኮ ከሞቀ ትዳርሽ ያፋታሻል:: ሰውን ሳይሆን ባልሽን እና እራስሽን አዳምጪ::
Jan 17, 2026