#religion ሰላም ✋ ስለ ኢትዮጽያ የአለም ብርሃን እባካችሁ ምታውቁትን ንገሩኝ ግራ ገባኝ ማለት እዛ ስብስብ ውስጥ ነበርኩ እና ምንፍቅና ነው ከዛ ውጪ ሚሉኝ ሰዎች በረቱ ከዛ ወጣሁ አሁን ግን እንዳጋጣሚ አንድ ልጅ እባክሽ እህት ተመለሺ አለኝ ብዙ ብዙ አለኝ ግን እውነት የትኛውን ማመን ከበደኝ እዚ ቻናል ውስጥ ያላችሁ (ኦርቶዶክስ) አማኞች እና በደንብ ምታውቁ እባካቹሁ ስለዚህ group ሆነ ብቻ ምታውቁትን ንገሩኝ🙏🙏🙏
Jan 08, 2026ምንም ጥያቄ የሌለው ምንፍቅና ነው። ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አንዳች እንከን የሌለባት በክርስቶስ ደም የተመሰረተች የክርስቶስ አካል ናት። ድኅነት ምናገኘው ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን በመፈጸም እና መልካም ስራ በመስራት ነው እንጂ በአንድ ከቤተ ክርስቲያን የተለየ የተሐድሶ ድርጅት አይደለም። ይሄ ግሩፕ ምዕመናንን ከቤተ ክርስቲያን በማስኮብለል እና ከሚስጥራተ ቤተ ክርስቲያን በማራቅ ድኅነታቸውን እንዲያጡ ሚያረግ የሰይጣን ወጥመድ ነው። እና በጭራሽ እንዳትሰሚያቸው እኅቴ ድኅነት ምናገኘው በቤተ ክርስቲያናችን ብቻ ነው። ቤተ ክርስቲያን ትናንትም አለች ዛሬም አለች ነገም ትኖራለች። የምንፍቅና ቡድን ወይም ማኅበር በጭራሽ ሊተካት አይችልም።
Jan 08, 2026