ቤት፣ መኪና ለመግዛት ለሚፈልግ ሁሉ ከባንክ ብድር ለማግኘት መስፈርቱ ምንድን ነው? የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቤት እና የመኪና ብድር ፈላጊዎችን የሚያስተናገዱበት በሚል ባወጣው መመሪያ መሰረት መጀመሪያ የተሰላው የ14 በመቶ የብድር ወለድ እንዳስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግበት እንደሚችል የተካተተበት ነው። በመመሪያው መሰረት፦ - ቤት ለመስራት ወይም ለመግዛት ቅድሚያ በብድር ከሚጠየቀው ገንዘብ 50 በመቶውን መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ - ለሚገዛው ወይም ለሚገነባው ቤት ከሚጠየቀው ብድር 200 በመቶ ዋጋ የሚያወጣ ቤት ባንኩ ማስያዣ ይፈልጋል፡፡ - በባንክ የሚያዘው ቤት መንገድና የተለያዩ መሰረተ ልማቶች የተነገቡበት አካባቢ ላይ ያለ መሆን አለበት፡፡ - ተበዳሪው በ10 አመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ብድሩን ለባንኩ መመለስ አለበት፡፡ - ከሶስት እስከ 6 ወራት በሚሰጠው የእፎይታ ጊዜም ጭምር ወለዱን (14 በመቶ) መክፈል ከተበዳሪው ይጠበቃል፡፡ - የተቀመጠው የ14 በመቶ የብድር ወለድ እንዳስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግበት ይችላል፡፡ ተበዳሪውም በተስተካከለው ወለድ መሰረት መክፈል ይኖርበታል፡፡
Jan 03, 2026