አንዴ እንዳታሳልፉት ቆይ ግን በዙውን ግዜ የባዶነት ስሜት ይሰማኛል ነገሮችን ማስተካከል ከበደኝ በቃ ልቤን ይጨንቀኛል ሰው ጋር መቀላቀል አልፈልግም ተስፋ ያረኩበት ነገር ጭራሽ ወፍ የለም ይህን ስሜት እነደት ላስተካክለው እስኪ መላ በሉኝ may be ያድኛችሁ ምክር አመለካከቴን ይቀይረው ይሆናል ይህ ደሞ ለኔ ትልቅ ደስታ ነው
Dec 30, 2025ብዙ ጊዜ ውስጣችን የባዶነት ስሜት የሚፈጠረው መንፈሳዊ ህይወታችን ላይ ያለ ክፍተት ነው ስለዚህ በቻልከው አቅም ለራስህ ጊዜ እየሰጠህ ከፈጣሪ ጋር ያለህን ነገር ተመልከት ከዛ በተጨማሪ ከቁሳዊው ዓለም ራስህን ገለል እያደረግክ ከተፈጥሮ እና ከራስህ ጋር ጊዜ ይኑርህ ከሶሻል ሚዲያ የፀዱ ጊዜያትን ከምትወዳቸው ከሚወዱህ ሰዎች ጋር አሳልፍ ችግሩን ባይፈታልህ እንኳን ለአእምሮህ ትንሽም ቢሆን ሰላም ይሰጠዋል
Dec 31, 2025