Hi guys.. I have one question እሱም ... እንዴት ነው ፍቅረኛ መያዝ ሚቻለው በጣምም introvert ነኝ ተቸገርኩ እንዴት ነው ምታወሩት እንዴት ነው ሚሆነው ደግሞም ሁሉም mind game አርጓታል ቁምነገረኝ የፍቅር ሴት የለም... እንዴት ነው ትክክለኛ የፍቅር አጋር ምታገኙት ? riz እንዴት ነው ምታረጉት ምክራቹን ሀሳባቹን please tell me... ሲቀጥል ደግሞ ቅድሚያ make the money ራስህ ላይ አተኩር ለውጥ ምናምን አትበሉ እሱ አልቸገረኝም!
Dec 30, 2025እኔ በግሌ በቅድሚያ ገንዘብ አግኝ ራስኽን ለውጥ ምናምን አልልኽም ! ስትለወጥማ የማይፈልግኽ የማይቀርብኽ የለም ኹሉም ይመኝሃል ያናገርከው ኹሉ እሺ ይልሃል ! በአንተነትህ ሳይኾን በስኬትኽ ይደምቃል . . . . ብዙ ብዙ ! ! እኔ ምን ጊዜም የምመርጠው የችግሬን ጊዜ ሴት ነው ! ባዶነቴን ሳትጠየፍ አብራኝ ሙሉ ልትኾን የምትደክመውን ! ይቺ ሴት ታዲያ ነገ አግኝቼ ባጣ ባዶነቴን ቀድማ ስለምታውቀው ፊቷን አታጠቁርብኝም ችግራችንን ዳግም እንደምንወጣው አምና ከጎኔ አትለየኝም ! ! so ለእኔም መጀመሪያ ገንዘብ ያዝ ምናምን የሚል ምክር አይጥመኝም ! ! ሌላው ግን እንዴት እውነተኛ ፍቅር እና ፍቅረኛ እንደምታገኝ አላውቅም ! ! ፈጣሪ ካልረዳኽ ከባድ ነው ! ! ሴት ሞልቷል የተለየች ሴት ማግኘት ግን ጾም ጸሎት ይፈልጋል !
Dec 30, 2025