ሰላም guys አዕምሮዬ በትናንት ውስጥ እየኖረ ውስጤን ሰላም ነስቶታል በቃ ዛሬን እየኖርኩ ደስተኛ ነገን እየኖርኩ ተስፈኛ መሆን አልቻልኩም ሁሌ ባለፈው አመታት ቀናት ወራት እና ሰዓታት ውስጥ በሰራውት ነገሮች ጥሩ ሆነ መጥፎ ሁኔታዎች ተወጥሬ ራሴን እየወቀስኩ እና እያዘንኩ ነው የምኖረው btw 22 አመቴ ነው ወንድ ነኝ እና በዚ ሁኔታ ውስጥ ያለፋቹ ሰዎች እንዴት ነው ዛሬን መኖር መጀመር የቻላቹት እንዴት ነው እስኪ መላ በሉኝ🙏
Dec 25, 2025የሎጥ ሚስትን ታሪክ ታውቀዋለህ ? ካላወከው በትንሹ ልንገርህ አስተማሪ የመፅሀፍ ቅዱስ ታሪክ ነው ! ። ሎጥ ከሚስቱ ጋር በሰዶም ከተማ ይኖር ነበር እና እግዚአብሔር ሰዶም እና ገሞራን ሊያጠፋ ወሰነ እና መላእክትን ልኮ ሎጥን ከቤተሰብህ ጋር ከከተማው ውጣ እና ወደ ሃላም አትመልከቱ ብሎ አዛቸው! ። ሎጥም ታዘዘ ወደኃላም አልተመለከተም ። ሚስቱ ግን ሰውነቷ ወጣ ፣ ልቧ ግን ቀረ !ወደኃላዋ ተመለከተች የጨው ሐውልትም ሆና ቀረች ይላል ። አንተም እንዲሁ ነህ ልክ እንደ ሎጥ ሚስት! ። እና እሷ ነገዋን ተስፋ ብታረግ ወዳለፈው ታሪኳ ባታይ ወይም ባትመለከት ነገዋን ብትናፍቅ እና ነገዋን ለመኖር ብትሄድ ኑሮ ጨው ሆና ባልቀረች ነበር ። እናም የማይጠቅምህ የሚጎዳህን ነገር ዞረህ አትይ አትመልከተውም ። በዚህ ታሪክ ሎጥ የኃላውን ባለመመልከቱ ህይወትን መረጠ ፤ ሚስቱ ያለፈውን ስለናፈቀች ጫው ሆና ቀርታለች ። አሁን ጥያቄው አንተስ ምን ትመርጣለህ ? ያው ነገን ነው አይደል ለእዛ ልብህ እና አዕምሮህ ከሰውነትህ በፊት ይጓዙ ።ያለፉት ነገሮች የሚጎዳም ወይም የሚጠቅምህም መስለውህ ቢታዩ ህ ተዋቸው ዙረህ አትመልከታቸው ። በተረፈ ፀሎት አድርግ ፈጣሪ ይርዳህ ። በጣም ፅሁፉን አረዘምኩት መሰል ለእሱ ይቅርታ🙏
Dec 25, 2025