#society
የ 11ኛ ክፍል ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪ ነኝ። በህጋዊ እና በይፋ መንገድ ሙሉ ስሜን መቀየር እፈልጋለው። ምክንያቱም ስሜ እና እኔ ልንገናኝ አልቻልንም። አሁን ላይ ለ ፋይዳም አልተመዘገብኩም፣ የልደት ካርድም አላወጣሁም ከቀበሌ (የተወለኩበት ሆስፒታሉ ድሮ ስለፈረሰ ፋይሌ ጠፍቷል።) የቀበሌ ID እና የትምህርት ዶክመንቶቼ እስከ 11ኛ አሉ። ትክክለኛው እድሜዬ 20 ሲሆን በ ሚንስትሪ ካርድ ከሄድን ደግሞ 18 ነው። እድሜም ማስተካከል እፈልጋለሁ በህጋዊ መንገድ። ቀጣይ አመት የ12ኛ ክፍል ዶክመንቴ በአዲሱ ስሜ እንዲሰራልኝ ከአሁኑ ሂደቱን መጀመር እፈልጋለሁ። ስለዚ ነገር ምታቁ ስዎች እባካችሁ የሆነ ነገር አሳውቁኝ
Dec 24, 20250 engagements