ቤተሰብ አግብታ የፈታች ፈልፈላ አለች እና በራሱዋ ቻት ማድረግ ጀመርን እና ከኔ ፍላጎት እንዳላት እየተሰማኝ ነው ታናሼ ነች። እና ጋይስ ባገባት ኖርማል ነው ብላቹ ታስባላቹ። በተለይ ከዚህ በፊት ምንም ሪሌሽንሺፕ ውስጥ እንዳልነበረ ሰው። ምንም የዘለቀ ሪሌሽንሺፕ ውስጥ አልነበርኩም ከሌላ ሰው ጋር። እና ሙስሊም ነኝ።
Dec 15, 2025አግባት መቼ? ሙስሊም ከሆነች፣ ዲኗን የምትጠብቅ ከሆነች፣ በፊት የነበረችበት ትዳር አንተ ላይ ተጽዕኖ የማያደርስ ከሆነ። ማለትም ያለፈ ባሏ እየመጣ የማያስቸግራችሁ ከሆነ (በአካል ብቻ አይደለም ሐቢቢ፤ በስልክም በሐሳብም እየመጣባት አሁናዊ ትዳራችሁን እንደሚያናጋው አትርሳ)፣ እሷም ወደዚያ ህይወት በሐሳቧም በአካሏም የማትሄድ ከሆነ፣ ከበፊቱ ባሏ የተለያዩበት ምክንያት ነገ አንተም ላይ የማይደርስ ከሆነ (ለምሳሌ ማግጣበት ካልሆነ...) አታግባት መቼ? ከላይ የተጻፉትን አንዱን እንኳ የሚጻረር ባህሪ ካላት + ነጭናጫ፣ "እኔ ነኝ ትክክል፣ ባል ልሁንብህ" አይነት ነገር ከሆነች፣ ባህሪዋ ከቤተሰብህ፣ ከስራህና ከራስህ የሚያጋጭህ ከሆነ ትቅርብህ። ስለውበት እና ገንዘቧ አላወራም! ያንን አይተህ ካገባሃት በቃ ሴት ያላየ ማንነትህን ወደ ምድራዊ ጀሀነም ቀየርከው ማለት ነው። ራዳርህ ማተኮር ያለበት ባህሪዋ ላይ ነው። በተረፈ ኢስቲኻራ ስገድበት። መልካም ቀን
Dec 16, 2025