ሰዎች በጣም የምወዳት ሴት በቃ ሁሉ ነገሬ የሆነቿ ሴት ለ 2 ዓመት ከ 8 ወር አብረን ቆይተን ለትዳር ዝግጅት ላይ ሆነን ያውም ከ 6 ወር በኋላ ሽምግልና ነው, ከዚህ በፊት በሌሎች ደባሪ ነገሮች ብዙ ነገር አልፊያት, ብዙ ጊዜ በተደጋጋሚ የምንጣላበት Best friend ነን የምትለውን ልጅ በጣም ታፈቅረው እንደነበር እና ልጁ ብዙም feeling ስላላሳያት /ሴትነቷ ይዟት መጠየቅ, ነገር ግን እስከአሁን በስልክም አለፍ ሲልም በአካልም እንደሚገናኙ ብታውቁ ምን ታደርጋላቹ? እንደሚያወሩ እና just normal talk እንደሆነ ትነግረኛለች ስገጣጠም ድንገት እንጂ ነግራኝ አይደለም So, ምን ልበል ምን ላድርግ? አጋጣሚ ከሁለት ቀን በፊት ነው በጣም የምታፈቅረው ልጅ እንደነበር የተረጋገጠ መረጃ ያገኘውት 🥺 she tell me she was virgin, በዛም ምክንያት 1ቀን በስህተት ነክቻት አላውቅም እና አሁን በሱ ልጅ ብዙ ጊዜ ተጣልተን ነበር እና ማውራት ማቆም አልቻለችም እንደነገርኳቹ Best F. ነን የምትለው still now, የኔ ጥያቄ ለምን በዚህ ልክ እኔን ደበቀች? ለምንስ ለኔ ስትል ስንት ነገር ትታ ይሄን መተው አቃታት, she loves him still now? ጭንቅላቴ ሊፈነዳ ነው ወገን ስራም መስራት አልቻልኩምኧረ አስረዱኝ የገጠማቹ ወንዶች, ሴቶችም ካለፋቹበት ሀሳብ ስጡኝ🙏
Dec 08, 2025የአንተ ጥፋት በልጁ ምክንያት በተደጋጋሚ መጣላት አልነበረብኽም ! አንድ ጊዜ ተይ ብለሃት ማቆም ካልቻለች አንተ ነበረክ ማቆም የነበረብኽ ! ! ምንም ጭቅጭቅ አያስፈልግም ። ከእኔ ባሕርይ አንጻር ልንገርኽ :- ወንድ best friend እንዳላት በነገረችኝ ወይም ባወቅኩበት ቅጽበት ምንም አይነት የስሜት መለዋወጥን ሳላሳይ ጓደኛሽ ደህና ነው በሚል እጠይቃታለው ( አስበኸዋል የእሱ ደህንነት አሳስቦኝ ስጠይቃት 😂 ይቺ ቀልደኛ ) እሱንም እሷንም እንደማይጠረጥር ኾኜ እንደሚገናኙና እንደማይገናኙ ከንግግሯ እረዳለው ሰላም እንድትልልኝም እነግራታለው ሰላምታዬን አድርሳለት ወንድ ልጅ ኾኖ ክብሩ ሲነካበት እንደማይወድ ኹሉ ፍቅረኛ እንዳላት አውቆ ሰላማዊ ሰላምታዬ እርቀትኽን ጠብቅ የሚል መልእክት እንዳዘለ ሳይረዳ ግንኙነታቸው ከቀጠለ ከእንግዲኽ እንዳታገኚው የሚል አንዲት ማስጠንቀቂያ ብቻ ከእኔ የሚወጣ ይኾናል ! ! ይቺን ቃል ተላልፋ ጥብቅና ልትቆምለት ብትሞክር አልፈው ተርፈው ከተገናኙና እንደ ቀድሞው ማውራታቸውን ከቀጠሉ brotherrrrr እሷን ማግኘት እየቻልኩ አላገኛትም በስልክ ማውራት እየቻልኩ አላወራትም ራሴን ከማያከብሩኝ ኹለት ሰዎች አርቃለው ! ! ተይ ብዬሽ አልሰማሽኝም ምናምን እያልኩ ተናግሬ መሄድን ራሱ አልመርጥም ! ዝምምምም ! ! ይኽኔ ጊዜ ስለማይሰጠኝ ምናምን ማለቷ አይቀርም እነዚኽ ወሬዎቿ ከሰላሜ ስለማይበልጡ ግድ አይሰጡኝም ኹለቱን በእኔ ዘንድ የተናቁ ኾነዋልና ! ! ( እንዲኽ ነው የማደርገው ያደረኩትም ) ( በነገርኽ ላይ ወደፊት ደግሞ በእሱ መገፋቴን አይቶ እግዚአብሔር ሰው ሰጠኝ ምናምን ትል ይሆናል 😂😂 ለእኔ የተሻለ ሊሰጠኝ እንደኾነ አይገባትም ) :- ስለዚኽ አንተ በዚኽ ደረጃ መጣላት አልነበረብኽም ። ቤተሰቧንና ገንዘቧን አካሏንም ልትሰጥኽ ትችላለች መንፈሷ ግን የአንተ አይደለም ! አንተ በድኗን ነው የምትታቀፈው እድሉን ሲያገኝ እሷም አካሏ በመንፈሷ ሲመራ ኹለቱም አንድ ቀን ይማግጣሉ ! ! ተወው መማገጥን እኔ የእኔ የምላትን ሴት ሌላ ወንድ አብሯት መተኛት አይደለም መሳሳምም አይደለም ሰላም ስትለው እንኳን በተለየ ኹናቴ እንድታቅፈው አልፈልግም ! ! ግን እመነኝ አንተ እንደምታቅፋት ጓደኛዬ ያለችውም ሰው ያቅፋታል ! ከአንተ ጋር እንደምትስቀው ከእሱ ጋርም ትስቃለች አንተን ወዬ እንደምትልኽ እሱንም ወዬ ትለዋለች አስበኸዋል እና የአንተ ወይም የእኔ ለእሷ ልዩ መኾን የቱ ጋር ነው ? አብሬአት ስለምተኛ ብቻ ? ? በጭራሽ እኔ እንደዚኽ አይነት ግንኙነትን አልፈልግም ! ! ያላከበረችኝን ሴት ላገባት አክብሬ ሽማግሌ ስልክ ታየኝ እኮ . . እና ምንም ልልኽ ነው ምንም አታለቃቅስ ሥራኽን ሥራ ! ዓለም ነጻ ገበያ ናት የወደድከውን የምትሸምትባት ! በፍቅር የምትገዛት ለፍቅርኽም የምትገዛለኽ ሞልታለች የአንዲት ሴት መምጣት መቅረት ሕይወትኽንና የእለት ተእለት ተግባርኽን እንዲያበላሽ አትፍቀድ ! ለፍቅር ብለኽ ልትዋረድ ትችላለኽ ፍቅር ባለበት ውስጥ ግን እመነኝ ትከበራለኽ። ዛሬ ቢሮ አልገባንም ረጃጃም ኮሜንቶችን እንጽፋለን ! !
Dec 09, 2025