Hey endet nachu please eski leyu tsega weyem ye ሀብተ ፈውስ yalachew abatoch Addis Ababa wust yet agegnalew
Dec 08, 2025የመድኃኔዓለም ክብር የተገለጠበት የፍኖተ ሕይወት ጉባኤ ተካሄደ! የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች የቅዱሳን ወዳጆች በ44ቱ ጸበል ቅድስት ሥላሴና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ህዳር 27 እና 28 ቅዳሜና እሁድ የፍኖተ ሕይወት ጉባኤያችን በሺህ የሚቆጠሩ የተወደዱ ክርስቲያኖች በተገኙበት በእግዚአብሔር ፈቃድ ጉባኤያችንን በደስታና በፈውስ በደስታ አሳልፈናል። በመድኃኔዓለም ኃይል አጋንንት የተደመሰሱበት በቅዱስ ዐማኑኤል የተባረክንበት የቅድስት ሥላሴ ጸጋና ፈውስን የተካፈልንበት ትዳር የዳነበት ብዙዎች ሕይወታቸው የተቀየረበት ብዙ ድንቅ ተአምራትና በረከትን ያገኘንበት ምስክርነት የተሰጠበት ድንቅ ጉባኤ ነበር። የጉባኤዎቹ የፎቶ ማስታወሻዎች በጥቂቱ ከላይ የተለቀቀውን ይመስል ነበር👆👆👆። ቀጣዩ ጉባኤያችን፦ የፊታችን ታህሳስ 4 እና 5 ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል። አድራሻ፦ከጎተራ ወደ ወሎ ሰፈር መሄጃ ወንጌላዊት ሕንጻ ጀርባ ወይንም ዘንባባ ሆስፒታል ጀርባ 44ቱ ጸበል ፈለገ ዮርዳኖስ ቅድስት ሥላሴ እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ጸበሉ ስፍራ። የቤተክርስቲያኑ አድራሻ Google map https://maps.app.goo.gl/Bgfd3G8QiRErw8k86 በሶሻል ሚዲያ ለመከታተል ከስር ያሉትን አማራጮች ይጠቀሙ፦ (Youtube– https://youtube.com@kesishenoktefera835) (Facebook–Kesis Henok Tefera page) (Telegram– https://t.me/kesishenoktefera) (Tik Tok– kesishenoktefera ይሄንን የመዳን መልእክት ለሌሎች ያካፍሉ። ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን። © መልአከ ሕይወት ቀሲስ ሄኖክ ተፈራ።
Dec 08, 2025