ለፕሮቴስታንት ወንድም እህቶች: 1) ጌታ ዮሐ 3 ላይ ለኒቆዲሞስ ዳግም ከውሃ እና ከመንፈስ ስለመወለድ የተናገረው ስለትክክለኛው ውሃ አይደለም የሚል ትምህርት ሰምቼ ነበር እቺን ብታስረዱኝ። 2) ት ዘካርያስ ላይ የእግዚአብሔር መልዐክ ስለእስራኤል እና ይሁዳ ከተሞች ምህረት ሲለምን ተፅፏል "70 አመት የተቆጣሀቸውን...የማትምራቸው እስከመቼ ነው...? ዘካ 1:12...ስለዚህ ቅዱሳን መላእክት እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ብቻ ባለፈ ስለሰው ልጆች ምህረት ቸርነት መለመን ይችላሉ ማለት እንችላለን? 3) 2ኛ 13:21 የሞተው ሰው የኤልሳዕ መቃብር ላይ ሲወድቅ ድኖ እንደተነሳ ይናገራል።ቅዱሳን ከሞቱም በኋላ ለሰው ልጆች ከእግዚአብሔር ዘንድ የምህረት ቸርነት መንገድ መሆን ይችላሉ ማለት እንችላለን? አመሰግናለሁ🙏
Dec 01, 2025ካነሳሀው አይቀርማ እስቲ በተጨማሪም 1. የዩሀንስ ወንጌል ምዕራፍ 5. ከ ቁጥር 1እስከ ቁጥር 6 ያለውን ብታስረዱን 2.ዜና መዋዕል ቀዳማዊ ምዕራፍ 5. ቁጥር 20 ላይ ለእግዛብሄር እና ለንጉሱ ሰገዱ ይላል ይህንንም ቃል ብታስረዱን ደስ ይለኛል
Dec 02, 2025