በክርስትናው ዓለም የሚታመንበት ነፃ ፍቃድ አለ።መፅሐፍ ቅዱስ በተለይም በዘፍጥረት የእግዚያብሔር የፈጠረውን ሁሉ "በጎ እንደሆነ አየ..." እያለ ይነግረናል።ስለዚህ በጎ የሚባል ነገር አለ።ነገር ግን መፅሐፍ ቅዱስ ስለክፋት የሚነግረን የለም።አሁን ጥያቄው መላእክትም ነፃ ፍቃድ አላቸው ለዛ ነው ሳጥናኤል የከዳው.....የመምረጥ መብት ከመሰጠቱ በፊት ደግሞ የሚመረጠው ነገር exist ማድረግ አለበት።አሁን ጥያቄው ለመላይክት ሆነ ለሰው ልጅ ነፃ ፍቃድ ከመሰጠቱ በፊት ምርጫቸው ተፈጥረው ነበር ወይ? ምርጫ ሳይኖር መችም የመምረጥ እድል አይኖርም።ስለዚህ look z first evil..."እኔ ፈጣሪ ነኝ ብሎ መታበይ " ወይም ደግሞ "የአዳም ፈጣሪ ለመሆን አለመታዘዝ" ከየት መጣ?....የእግዚያብሔር በጎ ነገርን ፈጠረ ካልን በዛ በጎ ልክና መጠን ያለውን ክፍት ደግሞ መፍጠር የሚችል ሌላ አካል አለ?.....ነፃ ፍቃዳችን ከgood በተቃራኒ የሆነውን evil የመፍጠር አቅም አለው?
Oct 15, 2020ጥያቄህ እንደገባኝ ከሆነ ኪሩቤሉ ሲፈጠር ጨለማ(ክፋት)ባይኖር አይመርጥም ነበር እና ያ ጨለማ ከየትመጣ ነው አ እሺ ምን መሰለህ ኪሩቤሎች ሕዝቅኤል በደንብ አንብበው....ና ኪሩቡ ድምፁ እንደ እግዜር ነበር ይላል ና የእግዚአብሔር ክብር የሚጋርዱ ናቸው ይላል....ከነዚህ ኪሩቦች አንዱ እግዚአብሔር በሰጠው በነዚ ነገሮች ልቡ ታበየ ይህ ማለት ምንድነው.....ከመለአክት እኮ እሻላለሁ፣ድምፄ የእግዚአብሔር ይመስላል..... እና እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ያየው ስለነበር እንደ እግዚአብሔር መሆን ከላል መሰለው ገብቶሀል አ ሀሳቤ ከዛ ይሄ እግዚአብሔር የመሆን ሀሳቡ ከጊዜ ወደ ግዜ እያደገ መጣ....ከዛ ተራረውን ብይዝ ዙፋኑ ላይ ብቀመጥ ና ለእኔ ቢሰግዱና ቢያመልኩን እግዚአብሔር መሆን ችላለው ብሎ ደመጀመ.....ይሄ ሁሉ ሲሆን -ሰው አልተፈጠረም -ጨለማ ሚባል ነገር አልነበረም .....እና መጨረሻ ላይ ይህንን ሀሳቡን ለማሳካት ስብከት ጀመረ(ሌሎች ኪሩባች እርሱን እን ዲያመልኩ መቀስቀስ ማለት ነው)የዚ ጊዜ እግዜር ከሱ አልፍ ሌሎችን ከተፈጠሩለት አላማ ዉጪ ሊያደርግ እንደሆነ ሲያይ....የሰጠውን -ክብር -የመኖር አላማ -ድምፁን እንዲሁም በውስጡ የነበረውን እሳት ወታ እንድትበላው አዘዘ.... የዚ ጊዜ ምን ተፈጠረ.....አላማ የሌለው፣በራሱ ምኞት የመደቀ ኪሩብ ብርሀኑ የተወሰደበት ና አመድ የሆነ ማንነት ያለው ሆነ..... ምንድነው እዚጋ ማወቅ ያለብህ እግዚአብሔር ብርሀን ነው በእርሱ ዘንድ ከቶ ጨለማ የለም... የኪሩቡ ብርሀን ሲወሰድ አላማ ቢስ ሆነ እንጂ አላማ ቢስነትን እግዚአብሔር አልፈጠረም ነገ የሌለው ህይወት ወይም ነገ ምን እንደሚሆን የማያውቅ ማንነት ያለው አካል ብርሀን የለውም ማለት ነው ብርሀን የሌለው ማንነት ደግሞ ጨለማ ነው......ጨለማ የተፈጠረ ነገር አደለም የብርሀን አለመኖር ነው እንጂ። ጥያቄህን መልሻለው ብዪ አስባለሁ... ግልፅ ያልሆነ ነገር ካለ መጠየቅ ይቻላል😊 በተረፈ ምነግርህ ነገረ ምንድነው ለሁሉም ጥያቄዎች መልስ ያለው መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው....ለነዚህ ጥያቄ ደግሞ ከኔ በበለጠ ሕዝቅኤል ቀስ ብለህ ደጋግመህ አንብበዉ
Oct 17, 2020