#personal
የእርቀት ትምርት ጀምሬ አሁን 12ኛ ነኝ እና ከሀገር ውጪ ነኝ ባሁኑ ጠቅልዬ ሀገር ገብቼ ትምርቴንም ልቀጥል አስቤ ነበር ግን ሰው ሳማክር ኧረ እዛው ይሻላል እኛም ኑሮ መሮናል እያሉ ያስፈራሩኛል ቤተሰቤ በኔ እጅ ነው ያሉት እዚ ደሞዜ 500$ ነው ምንም ስራ ጀምሬ ካልተሳካ ተቀጥሬስ ሀገር ላይ ብሰራ በቂ አይከፍሉም ከዚ ሀገር ከወጣሁ ደሞ መመለስ ስለማልችል መጨለሌ ነው እና ምን ትመክሩኛላቹህ ሪስኩን ወስጄ ልምጣ?
Nov 14, 20256 engagements