Can someone explain orthodoxy to me and the difference between catholic ,Protestantant and orthodox…I’ve been looking at Eastern Orthodoxy and I’m interested
Nov 10, 2025U can find ur answers on this book
Nov 11, 2025Can someone explain orthodoxy to me and the difference between catholic ,Protestantant and orthodox…I’ve been looking at Eastern Orthodoxy and I’m interested
Nov 10, 2025U can find ur answers on this book
Nov 11, 2025ሰላም እንዴት ነህ(ነሽ) ስለጠየክ በጣም ደስ ብሎኛል። ማውቀው ጥቂት ብቶንም ልንገርህ (ረጅም ነው ግን 🙄) ከቃሉ ብንጀምር ኦርቶ ማለት ቀጥተኛ እውነተኛ፡ ዴክሲያ (አስተምህሮ ፤ ስርዓተ አምልኮ) ስልዚህ እውውነተኛ ስርዓተ አምልኮ እምነት ማለት ነው፡፡ በዋናነት የሃይማኖት መግለጫችን ይህ ነው ይህን ጸሎተ ሃይማኖት ብለን ሁሌ እንጸልየዋለን (ኹሉን በያዘ፣ ሰማይንና ምድርን፥ የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ፡ አንድ አምላክ በሚኾን፡ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን። ዓለም ሳይፈጠር፡ ከእርሱ ጋራ በነበረ፥ አንድ የአብ ልጅ፥ አንድ ጌታ በሚኾን፡ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን። እርሱም፡ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፥ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ፥ የተወለደ እንጂ፡ ያልተፈጠረ፣ በመለኮቱ፡ ከአብ ጋራ የሚተካከል፣ ኹሉ፡ በእርሱ የኾነው፡ ኢየሱስ ክርስቶስ| ነው። በሰማይ ካለው፣ በምድርም ካለው፡ ያለእርሱ፡ ምንም ምን፡ የኾነ የለም። ስለእኛ ስለሰዎች፥ እኛን ለማዳን፡ ከሰማይ ወረደ፤ በመንፈስ ቅዱስ ግብር፡ ከቅድስት ድንግል ማርያም፡ ከሥጋዋ፡ ሥጋ፥ ከነፍሷ፡ ነፍስ ነሥቶ፡ ፍጹም ሰውን ኾነ። በጴንጤናዊው ጲላጦስ ዘመን፡ ስለእኛ፡ መከራን ተቀበለ። ተሰቀለ። ሞተ። ተቀበረ። በሦስተኛውም ቀን፡ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ። በክብር፥ በምስጋና፡ ወደሰማይ ዐረገ። በአባቱም ቀኝ፡ በዙፋኑ ተቀመጠ። ዳግመኛም፡ በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ፡ በምስጋና ይመለሳል። ለመንግሥቱ፡ ፍጻሜ የለውም። በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም እናምናለን። እርሱም፡ ሕይወትን የሚሰጥ፣ ከአብ የሠረፀና በነቢያት ዐድሮ የተናገረው፥ በሓዋርያት ላይ የወረደውና በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት፡ ዓለሙን፡ በጸጋው የሞላው፡ ቅዱሱ የእውነት መንፈስ ነው። ለእርሱም፡ ከአብና ከወልድ ጋራ፡ በአንድነት እንሰግድለታለን፤ እናመሰግነዋለንም። በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን። ኃጢኣት በሚሠረይባት፡ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን። የሙታን ትንሣኤ ተስፋ እናደርጋለን፥ በዘለዓለምም ሕይወት እናምናለን። ለዘለዓለሙ፤ አሜን።) ስለዚህ አንድ ኦቶድክሳዊ ይህንን የሚያምን ነው፡፡ ከሌሎቹ ቤተ እምነቶች ጋር በነገረ ክርስቶስ (በክርስቶስ አዳኝነት አምላክነት ) በነገረ ድነት በጣም ልዩነት አለን፡፡ ልምሳሌ ከፕሮቴስታንቱ ጋር በብዙ ልዩነት አለን ልምሳሌ ድነት Orthodox Christianity salvation is understood as a lifelong process called theosis (ሱታፌ አምላክ ), which is the ongoing transformation of a person into the likeness of God through communion with Him እኛ ድህነትን ምንረዳው በዚ ልክ ነው:: ስልዚህ It’s not “I was saved once,” but “I am being saved” and “I hope to be saved.” ለዚህ ነው ሂደታዊ ነው የምንለው ፡፡ በዋናነት ድኅነት ሶስት ደረጃዎች አሉት በመጽሃፍ ቅዱስ፡ ያለፈው 1)ድህነት(Justification) ይህ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በክርስቶስ በተደረገው የቤዛነት ስራ ከኃጢያትና ከሞት ፍርድ ነጻ መውጣታችን ነው፡፡ በጸጋ የምናገኘው ሲሆን ብጥምቀትና ብንስሃ የምካፈለው የመዳን መነሻ ነው፡፡ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ኤፌ 2፡8 ................. i think i need to make part 2 its saying character reached
Nov 11, 2025part 2 😂 1 ላይ የነበረው ያለፈው ድኅነት ነው እሽ (not only ድኅነት) 2)የአሁኑ ድኅነት በጸጋ የተቀበልነውን ነጻነት በህይወታችን ውስጥ በተግባር መግለጥ ያስፈልጋል በቅድስና ህይወት መመላለስ ያስፈልጋል፡፡ ይህም ክርስቶስን ወደ መምሰል ማደግ ነው፡፡ ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ ፊሊ 2፡12 እዚህ ጥቅስ ላይ መዳናችንን ለመፈጸም እንድንተጋ ይነግረናል ላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እንደርስ ኤፌ 4፡13 3)የወደፊቱ ድኅነት(glorification የመዳን ሂደት ፍጻሜ የሚያገኘው ክርስቶስ በክብር ሲመጣ ነው ያኔ ምዳናችን ይፈጸማል፡፡ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። ማቴ 24፡13 የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል። 1 ጴጥ ቅድም የጠቀስኩት ሱታፌ አምላክ() እግዚአብሄርን መሆን ይህንን የመዳን ትምህርት በደንብ ይገልጻል ይህም በባህሪይ እግዚአብሄርን መሆን ሳይሆን በጸጋ የእግዚአብሄር ባህሪይ ተካፋይ መሆን ማለት ነው፡፡ የቤተክርስቲያን ሚስጢራት በመዳን ሂደት ውስጥ ድርሻ አላቸው የምንለው ለዚህ ነው፡፡ BUT when we come to Protestantism salvation is a one-time event ይሄ በጣም ከብዙ በጥቂቱ ነው ፡፡ i recommend u to read more and ask watch this on yt (What Do Orthodox Christians Believe? - Mihret Melaku) beterefe ychame kabzawbsh sorry man
Nov 11, 2025Why am I Orthodox Christian? አንደ ከሌላ ቤተ እምነት(ሃይማኖት) ያለ ሰው ለምን አንተ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ሆንክ ቢላችሁ የምትመልሱት መልስ፦ ምክንያቱም:- 1).The Apostolic Faith-ሐዋርያዊ እምነት ስለሆነች፦ 👉 Orthodox is to be part of the One, Holy, Catholic and Apostolic Church founded by Christ and His Apostles. ኦርቶዶክስ በክርስቶስ እና በእርሱ ደቀመዛሙርት የተመሰረተች አንዲት፥ ቅድስት፥ ኩላዊት እና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ነች። 2). The True Understanding of Christ- ክርስቶስን በትክክል ስለምትረዳ ስለምታውቅ ወይም ክርስቶስ በትክክል ስለምትረዳ 👉 One United Nature of Christ or Fully Divine and Fully Human- Miaphysite Christology said that St. Cyril of Alexandria and others early Church Father. ክርስቶስ አንድ የተዋህደ ባህሪ (ስግው ቃል) ወይም ክርስቶስ ፍጹም መለኮት ፍጹም ሰው ነው! ቅ. ቄርሎስና ሌሎች የጥንቷ የቤተክርስቲያን አባቶች እንዳሉ 3). Orthodox Worship-ኦርቶዶክሳዊ(ሰማያዊ) እውነተኛ የሆነ አምልኮን ሰለምታመልክ፦ 👉The divine Liturgy follows of the early Church-የቀደመውን ቤተክርስቲያን የመለኮት ቅዳሴ ስለምትከተል 👉የጌታን ስጋና ደም እውነተኛ የጌታ ስጋና ደም ነው ብላ ስለምታምን ወይም ምልክት(ምሳሌ) አይደለም ስለምትል(ዮሐ 6፥48-56)- The Eucharist is not symbolic, but the real Body and Blood of Christ. 3). Apostolic Successions-ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ or The Key to Authenticity 👉የክህነት(የጵጵስና) ማዕረግ በሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ከቅዱስ ጴጥሮስ፥ ከቅዱሳን ሐዋርያት አንስቶ ሰለመጣልን፦ ማቴ 16፥18፤ 2ኛ ጢሞ 2፥2... 4). The Orthodox Path to Salvation- የድኅነት መንገዷ ትክክል ስለሆነ:- 👉Salvation is not a one time event, it is a lifelong journey- መዳን(ድኅነት) አንድ ጊዜ ክስተት ድርጊት አይደለም የእድሜ ልክ ጉዞ እንጂ ፊል 2፥12፤ ማቴ 24፥13... 5). The Orthodox Church and the saints- የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ቅዱሳንን በክርስትናቸውን ሕይወታቸውን መምሰል መከተልና በቅድስና መኖር፦ ዕብ13፥7፤ 1ኛ ጢሞ 2፥15፤ 1ኛ ጴጥ 5፥9... ...በእነዚህ ምክንያት ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ሆንኩ ለዛ ነው ነብዩ ኤርምያስ እንዲህ ያለ:- “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን፦ አንሄድባትም አሉ።” — ኤርምያስ 6፥16 ቅዱስ ይሁዳ ደግሞ እንዲህ አለ:- “ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።” — ይሁዳ 1፥3 ከቤተክርስቲያን ውጭ ያሉትን ከሃይማኖት የሚወጡት ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ አላቸው:- “መንፈስ ግን በግልጥ፦ በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው፥” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥1-2 👉👉👉እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግን እስከመጨረሻው እንማጸናለን ጸንተንም እንድናለን!!! “በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።” — ማቴዎስ 10፥22
Nov 11, 2025ይህን ምትረዳው በትውፊት እና በታሪክ ነው ይህም መጽሐፍ ቅዱስን ጠብቆ ያቆየ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያለው የትኛው ሃይማኖት ነው ሚለውን ትረዳለህ እነዚህን ጽሑፍ እና ኦድዮ አዳምጥ :- https://t.me/masyasorthodoxapologetics2017/41 https://t.me/Orthodox162127/693 ተጨማሪ የቤተክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ(አቡነ ጎርጎርዮስ) እና Church history ምናምን አንብብ
Nov 11, 2025Well orthodox uses primitive methods
Nov 11, 2025