ሰላም እንዴት አላችሁ ወገኖቼ ጥያቄው ለኦርቶዶክሳውያን በተለይ አብነት ትምህርት ለተማራችሁ ነው የኔ ጥያቄ ከዚህ በፊት ውዳሴ ማርያም አንቀጸ ብርሀን ተምሬአለሁ ግን ንባቡን ባውቀውም በቃሌ ልይዘው አልቻልኩም እና እንዴት እኝደምታጠኑ እንደምትሸመድዱ ንገሩኝ እስኪ እባካችሁ ቀጣዩን መልክእ ለመማር መጀመሪያ የተማርኩትን በቃሌ መያዝ አለብኝ እና እንዳይጠፋኝ አድርጌ የምይዝበት ቀለል ያለ ዘዴ ጠቁሙኝ ስለመልሳችሁ አመሰግናለሁ!!!! 🙏🙏🙏🙏
Nov 08, 2025ግራ የገባኝ የሰኞን በቃልህ ሳትይዝ እንዴት አንቀፀ ብርሃን ገባህ 🤔 ያለ መምህር እንዴት ተማርክ ምክንያቱም የሰኞን በቃልህ ሳትይዝ ወደ ማክሰኞ እራሱ አትገባም እንኳን አንቀፀ ብርሀን ወይስ ምንድነው ? ብቻ የመጀመሪያው ነገር ሁሉንም በአንድ ቀን ልያዝ ብለህ እንዳትጀምር ግማሽ ሉኩን ብቻ በደንብ ደጋግመህ ከልሰው በቃልህ የም ትይዝበት መንገድ 1የመጀመሪያው አቡነ ዘበሰማያት ፀልየህ ከቀልብህ ሆነህ ደጋግመው 2 ውሃ በደንብ ጠጣ አንዳንዶች ለብ ያለ ውሃ ይጠጣሉ 3 ግማሽ ሉኩን ከልሰህ እንደጨረስክ አቡነ ዘበሰማያት እና ሰላም ለኪ ደግመህ እንቅልፍህን ተኛ ከዛ ስትነቃ ተአምር ነው የምታየው እግዚአብሔር ይረዳሀል
Nov 08, 2025