Anyone who knows 22ቱን ሥነ ፍጥረታት clearly list argulgn please ?
Nov 06, 2025እንደ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮ 22ቱ ሥነፍጥረታትን ሁለት መጽሐፍት በተለያየ መልኩ ያስቀምጣሉ። የመጀመሪያው መጽሐፈ አክሲማሮስ ሲሆን በእዚህም መጽሐፍ በዕለተ እሁድ 8 ፍጥረታት ናቸው ይልና እነዚህም:- እሳት፣ ነፋስ፣ ውሃ፣ መሬት (ወይም 4ቱ ባሕርያተ ሥጋ)፣ ሰባቱ ሰማያት፣ መላዕክት፣ ጨለማ እና ብርሃን ናቸው። እስከ ጨለማ ያሉትን 7 ፍጥረታት በማሰብ (በሀልዮ) የተፈጠሩ ናቸው ይለናል። ሰኞ ከምድር እስከ 7ኛው ሰማይ የመላውን ውሀ ከሦስት ወገን ከፈለው ይለናል። ይሄንንም እንደ አንድ ፍጥረት ይቆጥረዋል። ማክሰኞ አዝርዕት፣ አትክልትና እፅዋት ተፈጥረዋል። ረቡዕ ከብርሃን ተከፍለው ጸሀይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ተፈጥረዋል። በዕለተ ሐሙስ ከባህር የተገኙ በደረታቸው የሚሳቡ፣ በእግራቸው የሚሽከረከሩና በክንፋቸው የሚበሩ ፍጥረታት ተፈጥረዋል። በዕለተ አርብ ከምድር የተገኙ እንስሳት፣ አዕዋፍት፣ አራዊት እንዲሁም የሰው ልጅ ተፈጥሯል። ስለዚህም እሁድ = 8፣ ሰኞ = 1፣ ማክሰኞ = 3፣ ረቡዕ = 3፣ ሀሙስ = 3፣ አርብ = 4 አጠቃላይ = 22 ሁለተኛው መጽሐፍ የብሉይ ኪዳን ትርጓሜ ሲሆን ይሄም ከመጽሐፈ ኩፋሌ ጋር የሚስማማ ነው። በዚህም መጽሐፍ የእለተ እሁድ ፍጥረታት ላይ ብርሃንን ከእሳት የተገኘ ነው ብሎ ቀንሶ 7 ያደርግና የእለተ ማክሰኞ ፍጥረታት ላይ የገነት እፅዋትን ጨምሮ 4 ያደርጋቸዋል። ሌሎቹን ከመጽሐፈ አክሲማሮስ ጋር ይጋራል።
Nov 06, 2025