Hey guys 👋 I’m a freshman student planning on studying law enam if there is anyone who have taken COC please help me out. How do I get ready for it?😭
Nov 03, 2025ሕግ አሪፍ ነው አሪፍ ምርጫ እኔ ብዙም ሳልጠይቅ ነው ዘው ብዬ የገባሁበት😁 የመጀመሪያ ኢንትራንስ ማለፍ ነው መስፈርቱ እሱን ደሞ አሳክተሽዋል boom🔥 ከዚህ በኃላ ያሉት ቀላል ናቸው መጀመሪያ ዩንቨርስቲ ገብተሽ እንደማንኛውም ተማሪ የመጀመሪያ semister freshman ከሁሉም እኩል ትወስጃለሽ 3 ወር አካባቢ ነው አንድ semister ለመጨረስ ከዛ የመጀመሪያ semister ከጨረሽ በኃላ ትምህርት ቤቱ ማስታወቂያ ያወጣል medicine መማር ለሚፈልጉና law መማር ለሚፈልጉ ብለው so law ለመግባት አንድ semister መማር ብቻ ነው🙌 ከዛ ያው ትመዘገቢያለሽ ቀን ይገልፁላችሁና የlaw መግቢያ ፈተና ይፈቱናችኅል ፈተናው እንደየዩንቨርስቲ ይለያያል ጠቅላላ እውቀት ስለሆነ ቀላል ነው ያው አንድ ማትቀር ጥያቄ አለች ለምን law ለመግባት ፈለግሽ ምትል እሷን interesting አርገሽ ትፅፊያታለሽ አሁን እኔ እሱን ጥያቄ መሳጭ ላርገው ብዬ "ሰፈራችን ውስጥ ባሏ አሲድ ደፍቶባት ከዛ በጠበቃ ሚከፈል ብር ቸግሯት ጠበቃ አቁማ ባለመከራከሯ 2 ወር ተፈረደበት እኔም ያኔ ቁጭት ይሁን ንዴት ባላቅም ውስጤ የጠበቃ ፍላጎት በቀለች"ብዬ ሰክሻለው ያው በጣም ባይሆንም መጠነኛ የእንግሊዘኛ እውቀት ያስፈልጋል መሰለኝ ሌላኛው ጥያቄ የፌደራል እና ዩኒተሪ ልዩነት ሌላኛው ደሞ የnegotiation mediation ምናምን መዘርዘር ነው 5 ጥይቄ ነበር ከ5ቱ ሶስቱን ነገርኩሽ አንዱ ጥያቄ ሳይገባኝ ነበር ዝም ብዬ የመሰለኝን የፃፍኩት አንዱ ጥይቄ ጠፍቶብኛል😂 ብቻ መግቢያ ፈተናው ይሄ ነበር ወደ ማርክ አያያዙ ልምጣልሽና Freshman የመጀመሪያ semister ከ50 ይያዛል ስለዚህ የመጀመሪያ semister ላይ እንዳታሾፊ law መመዝገብ ምችይው ለሴት ከ2.7 በላይ ለወንድ ደሞ ከ3. በላይ ነው ትምህርቱ ደሞ በጣም ቀላል ነው 3.9ቀልደሽ ታመጫለሽ(3.3 አምጥቼ ነው እኮ ምሰክስሽ😂 አይ ስቀልድ ነው እኔ ፈተና ነገ ሲሆን ስለማጠና እንዲህ ያመጣሁት እንጂ በጣም ቀላል ነው🙌) ይሄ ውጤትሽ ከ50 በጣም ከሰቀልሽው ሌላው ደሞ ኢንትራንስ ነው እሱን ከ20%ይይዙታል ስለዚህ ይሄ ዝቅ ቢልም በfreshman ታካክሻለሽ ሶስተኛው ደሞ መግቢያ ፈተናው ነው እሱ ደሞ ከ30 ነው ጥያቄውን እንደነገርኩሽ ቀላል ነው(እኔ 19 ነው መሰለኝ ያመጣሁት😂) ስለዚህ ከ100 አለቀ ማለት ነው የኛ ዩንቨርስቲ ማለፊያውን ከ70 አረገና እንደለመድኩት ተንጠልጥዬ 71 አግኝቼ አለፍኩ 156 ተማሪ ፈትኖ 49 ተማሪ አለፈ እኔ አለፍኩ አልልም አሳለፉኝ ነው ሆ😂 ሌላው law ከገባሽ በኃላ ለመመረቅ 5 ዓመት ይፈጅብሻል ከዛ ለ3 ዓመት ያህል ደኛ በመሆን በመንግስት ምደባ ስር ትሰሪያለሽ የ3 ዓመት የስራ ልምድ ሲኖርሽ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጠበቃ እንድትሆኚ የጠበቃ ፍቃድ ይሰጥሻል ከዛ እዚህ ላይ 2 ዓመት የስራ ልምድ ስትጨምሪበት በማንኛውም ፍርድ ቤት ጠበቃ ትሆኝ ዘንድ ፈተና ምናምን ተፈትነሽ ፈቃድ ይሰጥሻል So በማንኛውም የፌደራል ፍርድ ቤት ጠበቃ ለመሆን ከትምህርቱ ጋር 10 ዓመት ይፈጅብሻ😊 እንዳትፈሪ ደሞ😂
Nov 04, 2025