Question my orthodox people: አባታችን ሆይ ብለን ፀሎት ስንጨርስ ቅጥር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ብለን የምናደርሰው ፀሎት ከየት እንደወጣ ሚነግረኝ አለ? ከመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ቢሆን ደስ ይለኛል።
Oct 24, 2025እንግዲህ እኛ ተዋህዶ እንዳስተማረችን የተወደደች እናታችንን እንዲህ እያልን ከቃሉ ሳንወጣ በፀሎታችን እንጠራታለን እንዲህም እንላለን :- እመቤታችን ንፅህት ቅድስት ድንግል (ማቴ1:23) ማርያም ሆይ (2ቆሮ11:2) በመልአኩ በቅድስ ገብሬል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን (ሉቃ1:28) በሀሳብሽ ድንግል ነሽ (2ቆሮ 11:2) በስጋሽም ድንግል ነሽ (ማቴ1:23፣ህዝ 44:2) ያሸናፊ የልዑል እግዚአብሔር እናት ሆይ (ሉቃ 1:35) ሰላምታ ላንች ይገባሻል ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ (ሉቃ 1:28፣ሉቃ 1 :32) የማህፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው (ሉቃ 1:32) ፀጋን የተመላሽ ቅድስት ሆይ ደስ ይበልሽ ልኡል እግዚአብሔር ካንች ጋር ነውና (ሉቃ 1:28-30) ከተወደደው ከልጅሽ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታና ምህረትን ለምኝልን (1ቆሮ 5:20 በፅድቅ ስራ የኖሩት ይለምኑ ዘንድ ተሰጥቷቸዋልና) ሃጢአታችንም ያስተሰርይ ዘንድ ለዘላለሙ አሜን። እኛም ይህን ከመፀለይ ቸል ብለን የእናታችንን ውለታ አንረሳም፡፡
Oct 24, 2025