Werabe or ወራቤ hidu teblen neber i am medcine 5th year student selam new hageru rebsha ale sibal semeche neber gin i am not sure🤔🤔 If anyone has some information Please share me
Oct 21, 2025ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም ደረጃ ይውጣ ቢባል #ወራቤ ከተማ 1ኛ ላይ ነች ሐቢቢ። የዛሬ 4 አመት ነው አንዴ የተረበሸችው። እሱም የአማራ ክልል አሸባሪዎች መስጂድ ሲያቃጥሉና ሙስሊሞችን ሲገድሉ እዚህም አንድ ያለችውን ቤተክርስቲያን አመድ ያደረጉበት ክስተት ነው። መስመር የሳቱትን አደብ አስያዙ። ነፍስ አልጠፋም። የተጎዳውን ሆስፒታል አስገቡና በነጋታው ወደ ስራቸው ተሰማሩ። የሚገርምህ ያ የተቃጠለው የጭቃ ርብራብ ቤተክርስቲያን ዛሬ በብሎኬትና ሲሚንቶ ተደርጎ ተሰርቶ እንዴት እንዳመረበት! እንደ አጋጣሚ ከአመታት በኋላ ትናንት ወደዛ ሰፈር ለጉዳይ ሄጄ ነበር ያየሁት። በአጭሩ ምንም አይነት ረብሻ የለም። ስልጤ ዞን እንደ አማራ ክልል ረባሾች የሉባትም። ካሉም ቆንጠጥ ስለሚደረጉ ማንም ስለመረበሽ አያስብም። ይህን የምልህ እዚያ ከተማ ስለኖርኩ፣ ስለተማርኩ፣ ስለሰራሁ እና ቤተሰቦች ስላሉኝ ነው።
Oct 22, 2025